የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በጋምቤላ ክልል የሰብአዊ ድጋፎችን በእራስ አቅም ለመሸፈን ለተያዘው ግብ መሳካት  የባለድርሻ አካላት ትብብር ይጠናከራል  

Sep 4, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

‎ጋምቤላ፤ ነሐሴ 28/2018 (ኢዜአ) ፡-በጋምቤላ ክልል ሰብአዊ ድጋፎችን በራስ አቅም ለመሸፈን ለተያዘው ግብ መሳካት የባለድርሻ አካላት ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ገለጹ።

ተረጅነትን ለማስቀረት እየተከናወኑ ባሉት ስራዎችና በቀጣይ የበጋ መስኖ የግብርና ልማት ዙሪያ ያተኮረ የንቅናቄ ውይይት መድረክ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሄዷል።


ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ ለሚከሰቱ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ሰብአዊ ድጋፎችን በራስ አቅም ለመሸፈን ባለድርሻ አካላትን ያሳተፉ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በክልሉ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተቀየሱ እቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ ያለውን ሰፊ የመሬትና የውሃ ሀብት ካለው የሰው ኃይል ጋር አቀናጅቶ ለመጠቀም እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።

በዚህም ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ለሚያጋጥሙ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች በራስ አቅም ሰብአዊ ድጋፍ ለመስጠት የመጠባበቂያ የሰብል ምርትና የበጀት ፈንድ ላይ ትኩረት መሰጠቱን አስረድተዋል።

ምርታማነትን ከማሳደግ ጎን ለጎን ወቅት ጠብቆ ከማምረት ለመውጣት ለተነደፈው የበጋ ወራት የመስኖ ልማት ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ለዘርፉ ስኬታማነት በጋራ መረባረብ የሚገባ ሲሆን የግብአትና የባለሙያ ድጋፍ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ከመቼውም ጊዜ በላይ መስራት እንደሚገባ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው ገልጸዋል።

በክልሉ ሰብአዊ ድጋፎችን በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት የ400 ሚሊዮን ብር የመጠባበቂያ ፈንድ እቅድ ተነድፎ ንቅናቄ መጀመሩንም አስረድተዋል።


በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸኔ አስቲን በበኩላቸው፣ እንደ ሀገር ከተረጅነት ለመውጣት እየተተገበረ ላለው ኢኒሼቲቭ ውጤታማነት የመንግስትም ሆነ የድርጅቱ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ብለዋል።

በተለይ ሕብረተሰቡ ምርታማነቱን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንዲችል ያልተቆጠበ የድጋፍና የክትትል ስራዎችን ማከናወን የግድ እንደሚለው ነው የተናገሩት።

በንቅናቄ የውይይት መድረኩ ላይ የመንግስትና የድርጅት አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ አቅርቦትና መሰረተ ልማት በማስተሳሰር ለሰላምና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኝነቷን እያሳየች ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለማስተሳሰር የምታደርገው...

Oct 26, 2026

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎናል

ጎንደር ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የአካ...

Oct 20, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...

Oct 13, 2026

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል!

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...

Oct 13, 2026