የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ነገን በብልሃት ማነጽ - የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ

Sep 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

(በሙሴ መለሰ)

ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የጀመረችውን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ አጠናክራ ለመቀጠል እና ከጊዜው ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ለመራመድ “የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ስትራቴጂን በይፋ አድርጋለች።

ታኅሣሥ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው ይህ ታላቅ አገራዊ ዕቅድ፤ ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዓለም ከተመልካችነት ይልቅ ተሳታፊና መሪ የምትሆንበትን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።

ይህ አዲስ ስትራቴጂ ከቁጥሮች እና ከኢኮኖሚያዊ ስኬቶች ባሻገር፣ ዛሬን ከመቅረጽ ባለፈ ነገን ከመገንባት እና ለቀጣይ ትውልድ አሻራ ከማስቀመጥ አንጻር ሰፊና ጥልቅ ፋይዳ ያለው ሀገራዊ ትልም ነው።

በዲጂታል ዘመን የመረጃ ሉዓላዊነት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ ነው ። በዚህ ዘርፍ የሚያጋጥም ጥገኝነት የሃገር ደህንነት ላይም የራሱን አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳረፉ አይቀርም።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚህ ዙሪያ መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት እና ጠንካራ ሀገረ መንግሥት የሚገነባበት ቁልፍ የሉዓላዊነት ምሰሶ ነው ማለታቸው ይታወሳል።

የተዋሰ አሊያም በውጭ አካላት ላይ ጥገኛ የሆነ መረጃ ሀገራዊ መሻታችንን ማሳካት ስለማያስችል፤ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት ነውም ብለዋል።

የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ከወረቀት ባለፈ በህዝብና በሀገር ላይ የሚኖረው ተጨባጭ ማሳያ በአጭር ጊዜ ውስጥ መሬት የረገጠ እውነታ ነው።

ለአብነት ያህል፣ በዓለም ሁለተኛውና ለአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ ግንባታ መጀመሩ እና ከዩኤንዲፒ ጋር በመተባበር የተመረቀው 'AI UniPod' ማዕከል ለወጣቶች የተፈጠረ ትልቅ የቴክኖሎጂ መሠረት ነው።

ተቋማቱ ከሀገር ውስጥ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል በማመቻቸት ላይ መሆናቸው፣ ኢትዮጵያ የአህጉሪቱ የፈጠራ ማዕከል ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት የትውልድ አሻራ ነው።

የሞባይል ተጠቃሚዎችን ቁጥር 128 ሚሊዮን ለማድረስ እንዲሁም የ5G ኔትወርክ ተደራሽነትን ሙሉ በሙሉ እውን ለማድረግ የተነደፈው ዕቅድ፣ በከተማና በገጠር መካከል የነበረውን የዲጂታል ክፍተት በማጥበብ የመረጃ እኩልነትን የሚያረጋግጥ ትልቅ ምዕራፍ ነው።

እንደ ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከመሳሰሉ መሠረተ ልማቶች ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራው ይህ እቅድ፣ የዜጎችን ተደራሽነት በማስፋት እኩል እድል የሚፈጥር አሰራርን ይዘረጋል።

ይህ የዲጂታል መረብ መስፋፋት የዜጎችን ኑሮ በጥራት ከማሻሻል ባለፈ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲቀላጠፉ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

የመንግሥት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ ለማድረግ የሚከናወነው አሰራር ግልጽነትን በማስፈን በዜጎችና በተቋማት መካከል መተማመንን ያጎለብታል።

ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የዛሬን ስኬት ብቻ ሳይሆንየወደፊቱን ትውልድ አዕምሮ በዕውቀትና በፈጠራ ብርሃን በመቅረጽ የሀገርን የሰው ሀብት በዘላቂነት የሚያለማ የዕድገት ምሰሶ ነው።

ስትራቴጂው ካነጣጠረባቸው ቁልፍ ነጥቦች መካከል ተደራሽነትን ማስፋት፣ እኩል እድል መፍጠር እና በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ይገኙበታል።

ግልጽነት የሰፈነበት፣ ከወረቀትና ከቢሮክራሲ የጸዳ አሰራር መዘርጋቱ ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ላይ ያላቸውን እምነት ያጠናክራል። ይህ ደግሞ ማህበራዊ መተሳሰርን አጠናክሮ ለአንድነትና ለጋራ ብልጽግና መሰረት የሚጥል ትውልድ ተሻጋሪ ስራም ነው።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ሥራ ዕድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት የወጣቶችን ፈጠራ ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም መቀየር ያስችላል።

ወጣቱ በዲጂታል ንግድ፣ በሶፍትዌር ልማት እና በዲጂታል አገልግሎቶች ላይ ተሰማርቶ በራሱ ጥረት እያደገ ሲሄድ፣ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ መሠረት የጸና ይሆናል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ እያደገ ሲሄድ የሳይበር ደህንነት እና የመረጃ ጥበቃ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የሳይበር ደህንነት መሠረተ ልማቶችን ማጠናከሩን እንደ ዋና ዕቅድ ይዞ መንቀሳቀሱ ዜጎችና ተቋማት በአስተማማኝ ዲጂታል ምህዳር ውስጥ እንዲኖሩ ያስችላል።

ቴክኖሎጂ የሉዓላዊነት ሌላኛው መገለጫ በመሆኑ፣ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማትን ማስፋት ወሳኝ ነው። መረጃዎች በውጭ አካላት ቁጥጥር ስር ሲሆኑ የሀገር ደህንነት አደጋ ላይ ይወድቃል። የዲጂታል 2030 ስትራቴጂ የመረጃ ደህንነትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም በመፍጠር ለነገው ትውልድ የባለቤትነት ስሜት ያጎናጸፋል።

ወጣቶች በሮቦቲክስ፣ በዳታ ሳይንስ እና በሶፍትዌር ልማት ላይ ሲሰማሩ፣ ችግሮችን በፈጠራ ሃሳብ የሚፈቱ አዳዲስ ጅምሮች ይፈጠራሉ። ይህም የወጣቱን የእውቀት አቅምና ክህሎት ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ውጤት በመቀየር ለቀጣዩ ትውልድ ራሱን የቻለ የኢኮኖሚ መሠረት ይጥላል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ስኬትከተቀናጀ የመደመር እሳቤ ጋር የሚተሳሰር ነው። ነገን የተረጋጋ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ብልጽግና የምናረጋግጥበት ሁነኛ መንገድም ጭምር ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረግ ጥረት ይቀጥላል

አሶሳ፤ ጳጉሜን 5/2018 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን በማልማት ሁለንተናዊ እድገትና የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን የማድረ...

Sep 11, 2026

በመደመር መንግሥት ዕይታ አዲስ አበባን የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ) ፦በቀጣይ አምስት ዓመታት በዘላቂ የልማት ሥራዎች ላይ አፈፃፀማችንን በማላቅ ሕዝባችን የሰጠንን ሀላፊነት በብቃት መወ...

Aug 31, 2026

በአፋር ክልል የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ይጠናከራሉ

ሰመራ፣ነሀሴ 10/2018 (ኢዜአ):- በአፋር ክልል በተያዘው በጀት ዓመት የገቢ አማራጮችን የማስፋትና በቁርጠኝነት ገቢን የመሰብሰብ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚ...

Aug 17, 2026

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ ተደርጓል

ሸገር፣ ሐምሌ 18/2018 (ኢዜአ)፡-በሸገር ከተማ በተጠናቀቀው በጀት አመት አርሶ አደሩን በመደገፍ ምርትና ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታ...

Jul 27, 2026