🔇Unmute
ባህር ዳር ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በማፋጠን የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ትኩረት እንደሚሰጣቸው የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ።
የአማራ ክልል ምክር ቤት በመስራች መደበኛ ጉባኤው አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አደርጎ በድጋሚ መሰየሙ ይታወሳል።
ርእሰ መስተዳድሩ አቶ አረጋ ከበደ የመሰረተ ልማት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ባደረጉት ንግግር፤ የመሰረተ ልማት ግንባታን በሚፈለገው መልኩ ተግባራዊ በማድረግ በየዘርፉ ለውጥ ለማምጣት ይሰራል ብለዋል ።
በተለይ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማእድን፣ ቱሪዝምና ሌሎች የልማት ስራዎችን የሚያስፈልጉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ለማሟላት ያላሰለሰ ጥረት ይደረጋል ነው ያሉት።
በተጨማሪም የህዝብ ትስስርንና የንግድ ልውውጥን በማጠናከር ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠንም መሰረተ ልማቶችን የተሟላ ለማድረግ በላቀ ትጋት እንደሚሰራም አስረድተዋል።
በዋናነት መሰረተ ልማትን የማስፋፋት ስራ ላይ አስፈላጊውን መዋእለ ነዋይ በመመደብ የክልሉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማፋጠን በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
የመሰረተ ልማት ተቋማት ግንባታና የፋይናንስ አቅምን ለማጠናከርም የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎን የማሳደግ ስራ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለማስተሳሰር የምታደርገው...
Oct 26, 2026
ጎንደር ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የአካ...
Oct 20, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...
Oct 13, 2026
ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...
Oct 13, 2026