የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

በሲዳማ ክልል አመራሩ ለህዝብ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ትኩረት መስጠት አለበት

Oct 14, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ፤ጥቅምት3/2019(ኢዜአ):-በሲዳማ ክልል ከመሰረተ ልማት መጓተትና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት አዲሱ የክልሉ አመራር ትኩረት መስጠት እንዳለበት ነዋሪዎች ገለጹ።

በክልሉ ለሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።


የመደመር መንግስት ምስረታና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ክልል አቀፍ የውይይት መድረክ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅት ኢዜአ ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለጹት፣ የመደመር መንግስት ምስረታን ተከትሎ በየደረጃው የሚደረጉ ህዝባዊ ውይይቶች የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለይቶ ወደተግባር ለመግባት ያስችላል።

አዲሱ የክልሉ አመራር በተለይ ከመሰረተ ልማት መጓተትና ፍትሀዊ የልማት ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ የሚነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የሃገር ሽማግሌው አቶ ቶንጋላ ቶርጋ እንዳሉት የዛሬው መድረክ ከክልሉ አዳዲስ አመራሮች ጋር ለመተዋወቅና በልማት ሥራዎች ላይ የጋራ አቅጣጫ ለመያዝ ጠቀሜታ አለው።


አዲሱ የክልሉ አመራር የመንግስትና የህብረተሰቡን አቅም በማስተባባር ለህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት እንዳለበት ገልጸው፣ እንደነዋሪም ለክልሉ ልማትና እድገት መፋጠን የሚጠበቅብንን እንወጣለን ብለዋል።

በሃዋሳ ከተማ የሃዌላ ቱላ ክፍለ ከተማ ሴቶች ማህበር ሰብሳቢ ወይዘሮ ታየች አረጋ በበኩላቸው፤ የመንግስት ምስረታን ተከትሎ በየደረጃው እየተካሄዱ ያሉ ህዝባዊ መድረኮች በቀጣይ ስኬታማ የልማት ሥራ ለማከናውን የሚያስችሉ ናቸው።


ህዝቡ ከመሰረተ ልማት መጓተትና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች እንዳሉት አስታውሰው፣ እነዚህ ጥያቄዎች እንዲፈቱ አዳዲሶቹ የክልሉ አመራሮች በቁርጠኝነት መስራት አለባቸው ብለዋል።

የመደመር መንግስት በሃሳብ የበላይነት የሚያምን በመሆኑ መሰል ህዝባዊ መድረኮች መቀጠል አለባቸው ያሉት ደግሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)ን ወክለው በመድረኩ የተሳተፋት አቶ አቻ ለገሰ ናቸው፡፡


ህዝባዊ ውይይቶች የፖለቲካ ምህዳሩን ከማስፋት ባለፈ የህዝብን ትክክለኛ የልማት ጥያቄዎች ለይቶ ምላሽ ለመስጠት አቅም መሆናቸውን ጠቁመው፣ ለህዝብ የልማት ተጠቃሚነት ከመንግስት ጋር በመቀራረብ እንደሚሰሩ አመልክተዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መሳይ ኃይሉ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት ፤ በመደመር መንግስት ለህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት አቅጣጫ ተቀምጦ እየተሰራ ይገኛል።


በክልሉ ከልማት፣ ከመልካም አስተዳደር፣ ከፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ ከስራ ዕድል ፈጠራና መሰል ጉዳዮች ጋር የተነሱ የህዝብ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ታቅዶ ወደተግባር መገባቱንም ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም በክልሉ ያለውን የተፈጥሮ ጸጋ፣ የወጣቱን አቅምና የተለያዩ አካላትን ጭምር በማቀናጀት የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በውይይት መድረኩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መምሩ ሞኬ፣ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል!

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...

Oct 13, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...

Oct 13, 2026

ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮ-ኮደርስ ኢንሼቲቭ የዜጎችን ዲጂታል ክህሎት በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ የኢኖቬሽንና ቴክ...

Oct 4, 2026

የኢትዮ-ጅቡቲ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የሀገራቱንና የቀጣናውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ያጠናክራል- ምሁራን

አዲስ አበባ፤ መስከረም 16/2019 (ኢዜአ)፦ በጅቡቲ ዳመርጆግና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚዘረጋው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፕሮጀክት የ...

Sep 28, 2026