የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የደረጃዎች አጠቃቀም የምርትና የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና አለው

Oct 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የደረጃዎች አጠቃቀም የምርትና የአገልግሎት ጥራትን ከማሻሻል ባለፈ ንጹሕና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለው ኃይል ለማስፋፋት እንዲሁም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር መሰረት በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ።

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት በየዓመቱ የሚከበረውን የዓለም የደረጃዎች ቀን ዘንድሮ “ተመጣጣኝ ዋጋ ያለውና ንጹሕ ኃይል” በሚል መሪ ሐሳብ እያከበረ ይገኛል።


ቀኑን ምክንያት በማድረግም በጥራትና በደረጃዎች ላይ ባተኮሩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከአምራቾችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በማካሄድ ላይ ነው።

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት ዋና ዳይሬክተሯ መሰረት በቀለ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ደረጃዎች ንጹሕና ተመጣጣኝ ዋጋ ያለውን ኃይል ለማስፋፋት፣ የሀብት አጠቃቀምን ለማሻሻልና የኃይል አቅርቦትን በተቀናጀና በጥራት በተመሠረተ መንገድ ለማስተዳደር ቁልፍ ድርሻ አላቸው።

ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በመጠቀም በኃይል ማመንጨት ዘርፍ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆን እያደረገች ያለችውን ጥረት ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በታዳሽ ኃይል ልማት የተከናወኑ አበይት ሥራዎች ለዚህ ማሳያ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የኃይል ፍላጎት ከቴክኖሎጂያዊ፣ ከኢኮኖሚያዊና ከማኅበራዊ እድገት ጋር ተያይዞ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል።

ይህንን ፍላጎት ለማሟላት የሚደረጉ ጥረቶች ከደረጃዎች ጋር በተቀናጀ መንገድ መመራታቸው የኃይል አቅርቦትንና ቅልጥፍናን ከማሻሻሉም በላይ የሀብት ቁጠባን እንደሚያግዝ አብራርተዋል።

በተጨማሪም ደረጃዎች የማኅበረሰቡን ገንዘብና ጉልበት በመቆጠብ፣ የምርትና የአገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ እንዲሁም የሸማቾችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ የላቀ ፋይዳ እንዳላቸው አስረድተዋል።

በዚህ ረገድ የጥራት መሠረተ ልማት ተቋማት የሀገሪቱን የልማት ግቦች ለማሳካት የሚያስችሉ የጥራት ሥርዓቶችን በማስፋፋት፣ የምርትና የአገልግሎት ደረጃዎችን በማዘጋጀትና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት በኩል የሚያከናውኑት ተግባር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አመልክተዋል።

ኢንስቲትዩቱ ከ60 ዓመታት በላይ በተለያዩ አደረጃጀቶችና ስያሜዎች ሲሠራ መቆየቱን አስታውሰው የተቋሙን ሕጋዊና ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር፣ የራሱ የሆነ የደረጃዎች ሕግ እንዲኖረው ለማድረግ፣ አሠራሩን ለማዘመንና አገልግሎቶቹን ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ በርካታ የማሻሻያ ሥራዎች መከናወናቸውን አስረድተዋል።

የደረጃዎች ሥርዓት ውጤታማነት በተቋማት ወሰን ውስጥ ብቻ ሳይወሰን ለዜጎች ተጨባጭ ጥቅም ማስገኘት እንዳለበት ጠቁመው የሚከናወኑ ሥራዎች የማኅበረሰቡን ፍላጎት መመለስና የሀገሪቱን ዘላቂ ልማት ማገዝ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።


የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር መዓዛ አበራ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ የምርቶችን ጥራት ለማረጋገጥ የላብራቶሪ ምርመራ፣ የምርትና የሥራ አሠራር ሰርተፊኬሽን እንዲሁም የኢንስፔክሽን አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎቶችን በተለያዩ ከተሞች በማስፋፋት ለአምራች ድርጅቶች ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ መሆኑንም አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ምርቶች በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ገበያ ተቀባይነት እንዲያገኙ የጥራት ማረጋገጫና የደረጃዎች ማጣጣም ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።

የምርቶችን ጥራት ማረጋገጥ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ እንዳልሆነ ገልጸው፣ አምራቾች፣ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣናትና የሸማች ማኅበራት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ አቅርቦትና መሰረተ ልማት በማስተሳሰር ለሰላምና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኝነቷን እያሳየች ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለማስተሳሰር የምታደርገው...

Oct 26, 2026

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎናል

ጎንደር ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የአካ...

Oct 20, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...

Oct 13, 2026

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል!

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...

Oct 13, 2026