የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ሁለንተናዊ ልማትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል

Oct 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

መቱ ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦ የሀገር ግንባታንና ልማትን በማረጋገጥ የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) ተናገሩ።

በኦሮሚያ ክልል በተከናወነው አዲስ የዞኖች አወቃቀር መሠረት ለደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የተመደቡ አመራሮች በመቱ ከተማና በአጎራባች ወረዳዎች ከነዋሪዎች ጋር ትውውቅ አድርገዋል።


ዋና አስተዳዳሪው በወቅቱ በኦሮሚያ ክልል የተካሄደው አዲስ የዞኖች መዋቅር ዋነኛ ዓላማ የሕብረተሰቡን ሕይወት መቀየርና ከድሕነት ለማላቀቅ የሚያስችሉ አሰራሮችን ለመዘርጋት መደላድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል።

የሀገር ግንባታ እና ልማትን በማረጋገጥ የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ለማድረግ በተለይም ከተለመዱ የስራና የአሰራር ልማድና ባሕሎች መላቀቅ የግድ መሆኑን ዶክተር ረሻድ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ሁለንተናዊ ልማትና ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው በመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉንም የነቃ ተሳትፎና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ በመሆኑ የሕብረተሰቡ የልማትና የሰላም ተሳትፎ ተጠናክር እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በዚህም የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት በማረጋገጥ ተሰሚነቷን ይበልጥ ለማሳደግ በሁሉም መስኮች የሚሰራው ስራ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።


በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዲዳ ጉደታ በበኩላቸው፤ የህብረተሰቡ ጥያቄ የመሠረተ ልማት፣ የኢኮኖሚና የማሕበራዊ ልማት ተደራሽነና ተጠቃሚነት በመሆኑ ለዚህ ትልቅ ኃላፊነት ይጠብቀናል ብለዋል።

በአዲሱ አደረጃጀት የስራ ኃላፊነት የተሰጣቸው አመራሮችም የሕብረተሰቡንና የሀገርን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ አክለዋል።

የሕብረተሰቡን የኢኮኖሚ አቅም በማደራጀት ኑሮውን በማሻሻልና የኑሮ ውድነት ችግሮችን ለመቅረፍ አዲሱ የዞኖች መዋቅር የበለጠ ወደ ሕብረተሰቡ ለመቅረብ የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል።


የመቱ ከተማ ከንቲባ አቶ ተሻለ ኤጄርሶ፤ በክልል ደረጃ የተከናወነው የዞኖች አደረጃጀት ሁለንተናዊ ልማትና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል።

በአዲሱ መዋቅር የታሰበው ግብ እንዲሳካ የከተማ አስተዳደሩ በበለጠ ትኩረት ይሰራል ሲሉ ገልጸዋል።

አዲሱ የዞኖች አወቃቀር የዜጎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይበልጥ ወደሕብረተሰቡ በቀረበ መልኩ ይሰራል የሚል እምነት እንዳላቸው የገለጹት ደግሞ የመርሃግብሩ ተሳታፊ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ አቅርቦትና መሰረተ ልማት በማስተሳሰር ለሰላምና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኝነቷን እያሳየች ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለማስተሳሰር የምታደርገው...

Oct 26, 2026

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎናል

ጎንደር ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የአካ...

Oct 20, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...

Oct 13, 2026

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል!

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...

Oct 13, 2026