የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት

Oct 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ዛሬ የእንጦጦ ፒኮክ የወንዝ ዳርቻ ልማት አካል የሆነው፣ ከቀጨኔ በአምባሳደርና በኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትራችን ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል።

ይህ ታላቅ ልማት የአዲስ አበባን ውበት፣ የነዋሪዎቿን የኑሮ ጥራት፣ የከተማዋን የቱሪዝም መዳረሻነትና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያሳድግ ወሳኝ ሥራ ነው።

የወንዝ ዳርቻዎቻችንን ከብክለት፣ ከተፈጥሮ መራቆትና ከአደጋ ተጋላጭነት በማውጣት፣ ለአረንጓዴ ልማት፣ ለመዝናኛ፣ ለስፖርት፣ ለንግድና ለማኅበራዊ ትስስር ምቹ ስፍራዎችን እየፈጠርን ነው። ይህ ሥራ የወንዞቻችንን ተፈጥሯዊ ይዘት ከመመለስ ባለፈ፣ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ የበለጠ ምቹ፣ ማራኪና ለኑሮ የተሻለች እያደረጋት ነው።


የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ውጤቶች

ከቀጨኔ በአምባሳደርና በኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋው ይህ ፕሮጀክት 351 ሄክታር ስፋትና 10 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፣ የተለያዩ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችንና የሕዝብ መገልገያዎችን አካትቷል።

1. የተፈጥሮና የአካባቢ ጥበቃ

የአፈርና የውሃ ጥበቃ፣ የወንዝ ማጽዳት፣ የጎርፍ መከላከል፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን ማስፋፋትና የገጽታ ማስዋብ ሥራዎች ተከናውነዋል።

2. ዘመናዊ የመንገድና የእግረኛ መሠረተ ልማት

• 16 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፤

• 20 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤

• 22 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፤

• 5 ኪሎ ሜትር የመሮጫ ትራክ፤

• 18 የተሽከርካሪ ድልድዮች፤

• 23 የእግረኛ ድልድዮች ተገንብተው፣ ነባሮቹም ታድሰዋል።

3. ለስፖርት፣ ለመዝናኛና ለማኅበራዊ ትስስር የተዘጋጁ ስፍራዎች

ፕሮጀክቱ 12 የስፖርትና የጤና ማዕከላትን፣ ዘመናዊ የስፖርት ሜዳዎችን፣ ጂምናዚየሞችንና የፉትሳል ሜዳዎችን አካትቷል።

በተጨማሪም፦

• 21 የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎች፤

• 15 ፕላዛዎችና አምፊ ቲያትሮች፤

• 8 ፋውንቴኖችና የውሃ ትርዒት ማሳያዎች፤

• በተለያዩ አካባቢዎች የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች ተገንብተዋል።

4. የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የሥራ ዕድል ፈጠራ


የከተማችንን ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የሥራ ዕድሎችን ለማስፋት 30 ካፌዎችና 185 ሱቆች ተዘጋጅተዋል። የባንክ አገልግሎቶችም ተካትተዋል።

በወንዝ ዳርቻው አካባቢ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኑሮና የአኗኗር ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ የዕደ ጥበብ ምርቶች ማምረቻ፣ ማሳያና መሸጫ ማዕከል ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም የግብርና ምርቶችን ለማቅረብና ለመሸጥ የሚያስችል ማዕከል ተካትቷል።

5. የውሃ፣ የፍሳሽና የጎርፍ መውረጃ መሠረተ ልማት

የከተማ ዩቲሊቲዎችን ለማዘመንና የፍሳሽ አወጋገድ ሥርዓቱን ለማሻሻል፦

• 6 ኪሎ ሜትር የንጹሕ ውሃ መስመር፤

• 11 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር፤

• 12 ኪሎ ሜትር የጎርፍ መውረጃ መስመር፤

• 5 አነስተኛ ግድቦች፤

• 6 የውሃ ፍሰት መቆጣጠሪያ ግድቦች፤

• 3 የውሃ ማጣሪያ ማዕከላት ተገንብተዋል።

እነዚህ መሠረተ ልማቶች የውሃ ሀብታችንን ለመጠበቅ፣ የጎርፍ አደጋን ለመቀነስና የአካባቢውን ጤናማነት ለማሻሻል ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል።

6. ለዘላቂ ትራንስፖርትና ለአካባቢ ጥበቃ የተዘጋጁ መሠረተ ልማቶች

የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ምቹ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችን ለማስፋት 22 የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችና 8 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከላት ተገንብተዋል። እነዚህ ማዕከላት በአንድ ጊዜ ከ100 በላይ መኪናዎችን ቻርጅ ለማድረግ ያስችላሉ።

7. የከተማችንን ታሪክና ባህል የሚያስተዋውቁ መገለጫዎች

የወንዝ ዳርቻ ልማት ሙዚየምና “ወደ ምንጩ መመለስ (Back to Origin)” የተሰኘው ሐውልት የከተማችንን ታሪክ፣ ባህልና የተፈጥሮ ሀብት አስፈላጊነት የሚያስተዋውቁ ልዩ መገለጫዎች ናቸው። እነዚህም ተገንብተው ለአገልግሎት ተዘጋጅተዋል።

የልማታችን ዓላማ የሰው ሕይወትን ማሻሻል ነው!

የዚህ ልማት ዓላማ ውብ ስፍራዎችን መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ ለነዋሪዎቻችን ጤናማ አካባቢ፣ የመዝናኛ አማራጮች፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ መፍጠር ነው።

ተፈጥሮን ጠብቆ ማልማት፣ የከተማችንን ውስን የመሬት ሀብት ለሕዝብ ጥቅም ማዋልና የልማት ውጤቶችን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ የምንከተለው መርህ ነው።


የከተማችን ነዋሪዎች፣ እንኳን ደስ አላችሁ እላለሁ!

ይህ የጋራ ሀብታችን ነው። ስለዚህ ስፍራውን በንጽህና በመጠበቅ፣ አረንጓዴ ሀብቱን በመንከባከብና የተገነቡትን መሠረተ ልማቶች በአግባቡ በመጠቀም ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉን ሁላችንም የድርሻችንን እንወጣ።

አዲስ አበባን የተፈጥሮ ውበትና ዘመናዊ ልማት የተዋሃዱባት፣ ለነዋሪዎቿ የተሻለ ኑሮ የምትፈጥር ከተማ እናደርጋታለን!

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ አቅርቦትና መሰረተ ልማት በማስተሳሰር ለሰላምና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኝነቷን እያሳየች ነው

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለማስተሳሰር የምታደርገው...

Oct 26, 2026

የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ አድርጎናል

ጎንደር ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የአካ...

Oct 20, 2026

ኢትዮጵያ እና አይኤምኤፍ የሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...

Oct 13, 2026

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል!

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...

Oct 13, 2026