🔇Unmute
ሆሳዕና፤ ጥቅምት 18/2019(ኢዜአ):-የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄን በማሳካት ከድህነት ለመውጣትና አገራዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት እውን እንዲሆን ሙያዊ ሃላፊነታቸውን በቁርጠኝነት እንደሚወጡ የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።
ኢትዮጵያ ለባህር በር ካላት ቅርበት፣ ከነበራት የባለቤትነት ታሪክና ካላት የህዝብ ብዛት አኳያ ከባህር በር ተነጥላ እንድትኖር የሚያስገድድ ዓለም አቀፍ ህግ እንደሌለም ምሁራኑ አንስተዋል።
በዩኒቨርሲቲው የሰላምና ደህንነት ትምህርት መምህርና ተመራማሪው ተመስገን ቶማስ (ዶ/ር) እንዳሉት የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከድህነት በመውጣት ሉዓላዊነቷን በተሟላ መልኩ ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው።
ኢትዮጵያ በታሪካዊ ጠላቶቿ በተቀነባበረ ሴራ ከቀይ ባህር እንድትገለል መደረጓ ለሌላ ሀገር የባህር በር ጥገኛ አድርጎ ለከፍተኛ ወጪ እንትዳረግ አድርጓታል ብለዋል።
አሁን እየተነሳ ያለው የባህር በር የባለቤትነት ጥያቄ እውን መሆን የተሟላ ሉአላዊነቷን ለማረጋገጥና ከድህነት ለመውጣት የጀመረችውን ጥረት ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑን አመልክተዋል።
በዚህ በኩል ህዝብና መንግስት የጀመሩት ጥረት ለስኬት እንዲበቃ እንደ ምሁር የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም ተመስገን (ዶ/ር) ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድና በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ጥያቄዋ ምላሽ እንዲያገኝ የጀመረችው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና ለጋራ ተጠቃሚነት መረጋገጥ ጉልህ ሚና እንዳለውም ነው የገለጹት።
የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር ለመንግስት ብቻ የሚተው አይደለም ያሉት ተመስገን (ዶ/ር)፣ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄው በተለያዩ መመዘኛዎች በዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ መምጣቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ለዘመናት በባለቤትነት ስትጠቀምበት የነበረውን የባህር በር በሴራ እንድታጣ መደረጉን የተናገሩት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ጌታሁን አበራ ናቸው።
ኢትዮጵያ ለባህር በር ካላት ቅርበት፣ ከነበራት የባለቤትነት ታሪክ፣ ከህዝብ ብዛት አኳያ ከባህር በር ተነጥላ እንድትኖር የሚያስገድድ ዓለም አቀፍ ህግ እንደሌለም ገልጸዋል።
ጥያቄው የሰጥቶ መቀበል መርህን የተከተለ፣ ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት ካለው ፋይዳ በተጨማሪ የጋራ እድገትና ተጠቃሚነትን ያማከለ መሆኑ ተገቢነት አለው ሲሉም አክለዋል።
ኢትዮጵያ የዜጎቿን ክብርና ሕልውና የሚመጥን ስኬታማ ሜጋ የልማት ፕሮጀክቶችን ማከናወኗ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሚኖራትን ተደማጭነትና ተጽዕኖ ፈጣሪነት ከፍ ማድረጉንም መምሀሩ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለማስተሳሰር የምታደርገው...
Oct 26, 2026
ጎንደር ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ወደ ሥራ መግባት የአካባቢውን ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚ አድርጎናል ሲሉ የአካ...
Oct 20, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ትብብራቸውን ማጠናከር ያለመ የሁለትዮሽ ምክክር አድርገዋ...
Oct 13, 2026
ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥ...
Oct 13, 2026