
ሚዛን አማን፣ ታርጫ፣ ቦንጋ የካቲት 11/2017 (ኢዜአ )፡-በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ፣ ሚዛን አማንና ታርጫ ከተሞች እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የከተሞቹን ገጽታ በመቀየር ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እያደረጋቸው መሆኑን የከተማዎቹ ከንቲባዎች ተናገሩ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የኮሪደር ልማት ሥራ ከተሞችን ውብ፣ ፅዱና ለነዋሪዎች ምቹ ከማድረግ ባለፈ ለኢንቨስትመንትም ተመራጭ እንዲሆኑ እያስቻለ ነው።
ኢዜአ ያነጋገራቸው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚዛን አማን፣ የቦንጋ እና የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች እንዳሉት፣ ቀደም ሲል ከተሞቹ በፕላን ባለመመራታቸው የህብረተሰቡን የአገልግሎት ጥያቄ ለመመለስ እንቅፋት ሆኖባቸው ቆይቷል።
በሚዛን አማን ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የህብረተሰቡን የሥራ ባህልና የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ መምጣቱን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ግሩም ተማም ተናግረዋል።

በተጨማሪም የከተማዋ የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንዲጨምር፣ ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንድትሆንና ለነዋሪዎች ምቹ እንድትሆን እያደረጋት መሆኑን ገልጸዋል።
በከተማው ፕላን መሰረት የኮሪደር ልማት ሥራው እንደሚከናወን ለህብረተሰቡ ቀድሞ ግንዛቤ በመፈጠሩ በአሁኑ ወቅት የሥራ አፈጻጸሙ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ በበኩላቸው፣ የቦንጋ ከተማ ከተመሰረተች በርካታ ዓመታት ብታስቆጥርም የዕድሜዋን ያክል ባለመልሟቷ ውበቷ ተደብቆ መቆየቱን አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅት በከተማ አስተዳደሩ፣ በነዋሪውና በአጋር አካላት ተሳትፎ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ ከተማዋን ውብና ለኑሮ ምቹ እያደረጋት መሆኑ ጠቅሰዋል።
በዚህም በመጀመሪያው ዙር በ21 ሚሊዮን ብር የኮሪደር ልማት ሥራ መከናወኑን ጠቁመዋል።
የኮሪደር ልማቱ የመዝናኛ ፓርክ፣ የእግረኛ መንገድና እና ሌሎች አገልግሎቶችን ያካተተ መሆኑንም አብራርተዋል።

ከተማዋን የማስዋብ ሥራ መጀመሩን የገለጹት የታርጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዳዊት ወንድሙ በበኩላቸው፣ የኮሪደር ልማቱ የመንገድ አካፋዮች፣ የመንገድ ዳር መብራት ዝርጋታና የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን አካቶ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪ የእግረኛ መንገድና ሌሎች ልማቶች አካትቶ በተቀናጀ መንገድ የሚሰራው የኮሪደር ልማት ዘመን ተሻጋሪና መጪው ትውልድን ታሳቢ ያደረገ መሆኑንም ከንቲባው አክለዋል።
የከተሞቹ ከንቲባዎች ለኮሪደር ልማት ሥራው ስኬታማነት ህብረተሰቡ ንብረቱን በማንሳት ቦታውን ነጻ ከማድረግ ጀምሮ የተለያዩ እገዛዎችን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ድጋፍ በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026