
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2017(ኢዜአ)፡- ከተረጂነት በመላቀቅ የተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች የታሪክ እጥፋት የሚያመጡ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ ገለጹ።
ብልጽግና ፓርቲ ለሶስት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አጠናቋል።

ጉባኤው በሶስተኛ ቀን ውሎው ከተረጂነት አስተሳሰብ ለማላቀቅና የቤተሰብ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ተግባራዊ የሆነውን መርሃ ግብር አስመልክቶ በቀረበ የሱፐርቪዥን ስራዎች ሪፖርት ላይ ተወያይቷል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመረው ምርታማነትን የማሳደግ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።
በሀገር ደረጃ ተግባራዊ የተደረጉ እንደ ሌማት ትሩፋት፣ የከተማ ግብርና እና ሌሎች ኢኒሼቲቮች ማሳኪያ ግብ ሊሆኑ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ከተረጂነት የመላቀቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ስራው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ አመራሩ ለስራው የሰጠው ልዩ ትኩረት የሚበረታታ መሆኑን ነው የገለጹት።
ከተረጂነት መላቀቅ የአርበኝነት ምዕራፍ መሆኑን ያነሱት የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት፤ የቀጣይ ስራዎችን በፍጥነትና በመፍጠር መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል።
ከተረጂነት በመላቀቅ የተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች የታሪክ እጥፋት የሚያመጡ መሆናቸውንም አመላክተዋል።

በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የፖለቲካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብሩክ ግዛው የሱፐርቪዥን ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎች ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል።
መርሃ ግብሩን ማሳካት የሚያስችል ዕቅድ መዘጋጀቱን፣ የመግባባት ስራ በሁሉም ደረጃ መሠራቱን እንዲሁም ተጠቃሚዎች ከተረጂነት ለመውጣት ትክክለኛ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
በተለይም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት በየደረጃው እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች አበረታች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በሴፍቲኔት መርሃ ግብር ተጠቃሚ የሆኑ ዜጎች ዕድሉን በአግባቡ ተጠቅመው ከተረጂነት እንዲላቀቁ እየተደረገ ያለው ርብርብ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
የንቅናቄ ስራው በሁሉም አካባቢዎች ያለው የግንዛቤ፣ የአመለካከትና የዝግጁነት ወጥነትን ማስተካከል እንደሚገባም ተናግረዋል።

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር)፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የመሸጋገር ሂደት ከሃሳብ ወደ ተግባር መሸጋገር መጀመሩን ተናግረዋል።
ተረጂነትን ከመቅረፍ አኳያ ሰፊ ስራ መሰራቱን ጠቁመው፤ ክልሎች የመጠባበቂያ እህል ክምችትን ለማሳደግ መሠራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
አመራር አባላት ግብዓቶችን ለአርሶ አደሮች ተደራሽ ከማድረግ አኳያ ሰፊ ስራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) በበኩላቸው ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።
የመጠባበቂያ እህል ክምችትን ማሳደግ ከሁሉም በላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ተግባራዊ መደረግ እንዳለበትም ጠቁመዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በበኩላቸው፤ በከተማ ሴፍቲኔት የታቀፉ ዜጎች ሰርተው ራሳቸውን እንዲችሉ የቁጠባ ባህላቸው እንዲያድግ ሥራዎች እየተከናወኑ ናቸው ብለዋል።
በዚህም በተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ለሌሎች አርዓያ መሆን የሚችሉ ዜጎች ማውጣት መጀመሩን ጠቁመዋል።
በውይይቱ ተሳታፊዎች በሁሉም ክልሎች ከተረጂነት ለመላቀቅ የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ጠቁመው፤ የታለመውን ዓላማን ከግብ ለማደረስም ተጨማሪ ርብርብ እንደሚደርግም አብራርተዋል።
ጅማ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ተናገሩ...
Apr 24, 2026
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መ...
Apr 22, 2026
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...
Apr 15, 2026
አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...
Apr 9, 2026