
ጅማ፣ መጋቢት 01/2017 (ኢዜአ)፦ ከ699 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥረው ሶስተኛው የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በተገኙበት በጅማ ከተማ ይፋ ሆኗል።
ሚኒስትሯ በማስጀመሪያ መርሃ ግብር እንዳሉት ፕሮጀክቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን ህይወታቸውን ያሻሽላል።
ለቀጣይ ሶስት ዓመታተ የሚተገበረው ፕሮጀክቱ በሀገሪቷ በተለያዩ ከተሞች ከ699 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የሚያመቻችና ብዙዎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት የሚቀይር መሆኑን ገልጸዋል።
ባለፉት ዓመታት በልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ ተተግብሮ ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል ብለዋል።
ፕሮጀክቱ ከኮሪደር ልማት ጋር ተጣጥሞ እንደሚተገብር ገልፀው፤ ከተሞቻችን ውብ፤ ጽዱና አረንጓዴ ሆነው ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እንዲሆኑ በትብብርና በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን አንስተዋል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀመር በበኩላቸው ልማታዊ ሴፍትኔቱ ለከተማችን ውበት አጋዥ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችን የስራ እድል በመፍጠር ሕይወታቸውን የሚለውጥ ነው ብለዋል።
ከዚህ በፊት የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ተጠቃሚ የነበሩ ነዋሪዎች በበኩላቸው በቆይታቸው ሰርተው ካገኙት ገንዘብም ቆጥበው መለወጣቸውን ለአብነት አንስተዋል።
በዚህ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የ88 ከተሞች አመራሮች እና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026