የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

5ኛው የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤና አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

May 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 29/2017(ኢዜአ)፦ 5ኛው የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤና አውደ ርዕይ ከግንቦት 7 እስከ 9/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሸሪፍ ሚያን ገለጹ።

አምባሳደሩ በሰጡት መግለጫ፥ በንግድ ልማት ጉባኤና አውደ ርዕዩ ላይ ከ100 በላይ የፓኪስታን አምራች ድርጅቶች ይሳተፋሉ ብለዋል።

ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የንግድ ትስስርን የሚያጠናክሩ የሕክምና መድኃኒት ምርትና መሣሪያዎች፣ የውበትና ቆዳ እንክብካቤ ውጤቶች፣ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ምርቶች፣ የምግብና የምግብ ነክ የግብርና ምርቶች፣ የአውቶሞቲቭ መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሪክና የቤት እቃዎች በአውደ ርዕዩ እንደሚቀርቡም ገልጸዋል።

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር፥ የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የፓኪስታን ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ፈሰስ እንዲያደርጉ ተነሳሽነት እየፈጠረ ነው ብለዋል።

ባለሀብቶቹ በግብርና ማቀነባበር፣ በጨርቃጨርቅ፣ በሕክምና እና ሌሎች የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዲሳተፉ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

5ኛው የፓኪስታን አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤና አውደ ርዕይ በኢትዮጵያና ፓኪስታን መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አንስተዋል።

በፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤና አውደ ርዕይ የአፍሪካ ሀገራት እና የፓኪስታን መንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የንግድ መሪዎችና ባለሃብቶች የሚሳተፉ ሲሆን፥ ዝግጅቱም የንግድና ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የንግድ ልማት ጉባኤ፣ የሁለትዮሽ የንግድ ውይይቶች፣ የመንግስት ለመንግስት የምክክር መድረኮችን ጨምሮ የተለያዩ ሁነቶች እንደሚካሄዱም ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026