
አዲስ አበባ፤ግንቦት 21/2017(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እየተገነባ ያለው ጠንካራ የፋይናንስ ሥርዓት ለኢንሹራንስ ዘርፉ አስተማማኝ መሰረት የሚጥል መሆኑን የአፍሪካ ኢንሹራንስ ድርጅት ፕሬዚዳንት ፓቲ መርቲን ገለጹ።
ፕሬዝዳንቷ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፉ ላይ እያደረገችው ያለውን የሪፎርም ስራ አድንቀዋል።
በተለይም በሀገር አቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የፋይናንስ ዘርፉን ጠንካራና አስተማማኝ ለማድረግ የወሰደቻቸው የህግና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ለውጥ በመፍጠር ውጤታማ መሆናቸውን አንስተዋል።
ሀገሪቷ ጠንካራ የፋይናንስ ሥርዓት ለመገንባት እያደረገችው ያለው ጥረት ለኢንሹራንስ ዘርፉ ዕድገትና ቀጣይነት መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።
በአፍሪካ የኢንሹራንስ ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ ዕድገት ባያስመዘግብም ኢትዮጵያን ጨምሮ አንዳንድ ሀገራት በዘርፉ በትኩረት እየሰሩበት መሆኑ ተስፋ ሰጪ ነው ብለዋል።
የኢንሹራንስ ገበያውን ተደራሽነት ለማስፋትም የፋይናንስ ሥርዓቱን ማጠናከር ወሳኝ ሚና እንዳለው ነው ያብራሩት።
የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ዓለምን እየፈተኑ መሆኑን አንስተው፥ ለዚህ ደግሞ በቂ ምላሽ የሚሰጥና አደጋን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችሉ የኢንሹራንስ ተቋማትን መገንባት ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ከአስተናገደችው የአፍሪካ ኢንሹራንስ ጉባኤ በተጓዳኝ ከተለያዩ የኢንሹራንስ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጋር በዘርፉ ስለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችላይ ውይይት ማድረጋቸውንም ፕሬዚዳንቷ አንስተዋል።
በቀጣይም በአፍሪካ የኢንሹራንስ ዘርፉ ለአጠቃላይ ምጣኔ ሃብታዊ ዕድገትና ለህዝቦች ተጠቃሚነት ሚናውን እንዲያሳድግ እንሰራለን ነው ያሉት።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026