
ሐይቅ ፤ ሰኔ 28/2017(ኢዜአ) ፡-በሐይቅ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የማንሰራራት ጉዞ ሂደቱን የሚያጠናክር ነው ሲሉ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) አስታወቁ።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የክልልና የደቡብ ወሎ ዞን አመራሮች የሐይቅ ከተማ የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅት ምክትል ርዕሰ-መስተዳድሩ አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) ፤ ዛሬ በሐይቅ ከተማ የተመለከትነው የኮሪደር ልማት ጅምር ስራ የማንሰራራት ጉዞ ሂደቱን የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
የኮሪደር ልማቱ የከተማውን ገጽታ ይበልጥ ውብ በማደረግ ለነዋሪዎች፣ ለጎብኚዎችና ለኢንቨስትመንት ምቹ ማድረግ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል።
የሐይቅ-ቢስቲማ-ጭፍራ መንገድና በገበታ ለትውልድ እየተገነባ ያለው የሐይቅ ሎጎ ፕሮጀክት የከተማዋን እድገት በማፋጠን የቱሪስት መዳረሻ እንድትሆን የሚያስችል መሆኑንም ገልጸዋል።
መንግስት ከሕዝብ ጋር ተቀናጅቶ ኮሪደርን ጨምሮ ሌሎቸንም የልማት ተግባራት እያከናወነ በውጤታማነት በመቀጠል የብልፅግናን ጉዞ እያሳካ መሆኑን አስረድተዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ መኮንን በበኩላቸው፤ በዞኑ ስር በሚገኙ ሶስት ከተሞች የኮሪደር ልማት እየተከናወነ ነው ብለዋል።

የሐይቅ ከተማ የኮሪደር ልማት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ በተያዘለት ጊዜና ጥራት ለማስፈፀም ተገቢው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የከተማውን የኮሪደር ልማት ሥራ እስከ ታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር መሀመድ ናቸው።

ልማቱ የእግረኛና የብስክሌት መንገድን እንዲሁም አረንጓዴ ሥፍራና መዝናኛዎችንም ያካተተ ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026