
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦ ሶስተኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም የገበያ ትስስር ለመፍጠርና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ማሳደግ የሚያስችል ልምድ እንዲያገኙ ማስቻሉን በፎረሙ በተከፈተው ኤግዚቢሽን የተሳተፉ አምራቾች ገለፁ።
ላለፉት ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ዛሬ ተጠናቋል።
የማጠቃለያ መርሃ ግብሩም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ የአፍሪካ ሚኒስትሮች፣ ሥራ ፈጣሪዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል።
በፎረሙ ላይ ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡ በማምርቻው ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶች እንዳሉት ፎረሙ የገበያ ትስስር የፈጠሩበትና የተሻለ ልምድ ያገኙበት ነው።
ከአምራቾቹ መካከል የቆዳ ውጤቶች ማምረት ሥራ ላይ የተሰማሩት ሶስና ሲሳይ፥ ከዚህ ቀደም የቆዳ ውጤቶችን ገዝተው ሲሸጡ መቆያተቸውን አውስተዋል።
ከሁለት ዓመት ወዲህ የቆዳ ምርቶችን በእጅ በመስራት ወደ ገበያ ማቅረብ የጀመሩ ሲሆን ከራሳቸው አልፎ ለስድስት ሰዎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ገልፀዋል።
ፎረሙ በዘርፉ የተሻለና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉበት ልምድ ማግኘታቸን ነው ያስረዱት።
ለሁለት አስርት ዓመታት የሚጠጋ ጊዜ ተቀጥረው ሲሰሩ የቆዩት ጌጤ አስፋው በበኩላቸው ለወትሮው ለራሳቸውና ለሚቀርቧቸው ሰዎች የሹራብ አልባሳትን በስጦታ መልክ ሰርተው ያቀርቡ እንደነበር ተናግረዋል።
አሁን ላይ ሶስት ሆነው በመደራጀት የጀመሩት ቢሊሌ የሹራብ አልባሳት ስራ አድጎ፥ ለአራት ሰዎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠሩን ጠቁመዋል።
የአፍሪካ ሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም የገበያ ትስስር ከመፍጠር ባለፈ ልምድ እንዲለዋወጡና የላቀ መነሳሳትን እንዲፈጥሩ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።
ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ባህላዊ አልባሳትን መስራት የጀመሩት የዕለት ገብረአብ፥ አሁን ላይ 5 የቤተሰብ አባላትን በሙያ አሰልጥነው ወደ ስራ ማስገባታቸውን ነው ያነሱት።
የተለያዩ አልባሳትና የደንብ ልብሶችን ላለፉት 9 ዓመታት በማምረት ለገበያ ሲያቀርብ የቆየው የሎዛ ጋርመንት ምክትል ስራ አስኪያጅ ገነት ጥላሁን በበኩላቸው፥ አሁን ላይ ከ20 በላይ ለሆኑ ሰዎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል።
ፎረሙ ምርቶቻቸውን የተሻለ ማድረግ የሚችሉበት ተሞክሮ ያገኙበትና የሀገር ውስጥ ምርትን ለማበረታታት አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል።
አምራቾቹ በተለይም ወጣቶች ከጠባቂነት ይልቅ ስራ ፈጣሪ ለመሆን ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ ስራ ላይ አተኩረው እንዲሰሩም መክረዋል።
አሁን ላይ ያለውን ሰፊ የስራ እድል በመጠቀም ስራ ፈጣሪ በመሆን ራን፣ ቤተሰብን እና ሀገርን ለመጥቀም ተግቶ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026