
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ከተማን የመንገድ መሰረተ ልማት በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞችና በየደረጃው የሚገኘው አመራር የበለጠ መትጋት እንዳለባቸው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2017 በጀት አመት በመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታው መስክ ለተገኘው ስኬት ለሰራተኞቹ የምስጋናና የእውቅና መርሃ-ግብር አካሂዷል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ላይ ከንቲባዋ እንደገለጹት የከተማዋ የመንገድ ሽፋን ገና ብዙ መስራትን የሚጠይቅ ነው።

በዚህ ሒደት የባለስልጣኑ ሰራተኞች አሁን ለተደረሰበት ደረጃ ያሳዩት ትጋትና የስራ ተነሳሽነት የሚያስመሰግናቸው እንደሆነ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
ከተማችን አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እስከምትሆን ድረስ 24/7 ነው የምንሰራው ያሉት ከንቲባዋ ለሰራተኞቹ የተሰጠው እውቅና እና ምስጋና የበለጠ ሞራል ሆኖ የተሻለ ለመፈጸም እንደሚያነሳሳ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ሰራተኞቹ እስከዛሬ ያሳዩትን ትጋት የበለጠ በማጠናከር ለከተማዋ የመንገድ ሽፋን እድገት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በበጀት አመቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ብዙ ቅሬታ የነበረባቸውን ፕሮጀክቶች በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃቱን ያስታወሱት ደግሞ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሙህዲን ረሻድ ናቸው።
አሁን ለተገኘው ውጤትም በትጋት የሰሩት የባለስልጣኑ ሰራተኞችና አመራሮች ምስጋና እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በ2017 በጀት አመት ከፍተኛ የህዝብ የመልካም አስተዳደር ቅሬታ ሲነሳባቸው የነበሩትን ጨምሮ 31 ነጥብ 5 ኪሎሜትር ርዝመት ያላቸው 13 የመንገድ ፕሮጀክቶች እና 8 ድልድዮች ተጠናቀው ለምረቃ እንዲበቁ ማድረጉ ተገልጿል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026