
ባሌ ሮቤ ፤ ሐምሌ 13/2017 (ኢዜአ)፡- ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሲያደርጉት የቆዩትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የባሌ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
የባሌ ሮቤ ከተማን ጨምሮ የዞኑ የሕዝብ ተወካዮችና አመራሮች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዋንጫን ከምዕራብ አርሲ ዞን ዛሬ ተረክበዋል።
ርክክብ የተካሄደው የሕዳሴ ግድብ ዋንጫ በዲንሾ ከተማ ደማቅ አቀባበል ከተደረገለት በኋላ ነው።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከታደሙት ነዋሪዎች መካከል አቶ ሐሰን አህመድ በሰጡት አስተያየት፤ ኢትዮጵያዊያን የአንድነት አርማ ለሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ከፍጻሜ ለማድረስ በስጦታና በቦንድ ግዥ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
አሁንም የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያና የጋራ አሻራ የሆነው የሕዳሴ ግድብ ከዳር እንዲደርስ በገቢ አሰባሰብ ሂደቱ የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያዊያንን የይቻላል መንፈስ ዳግም ያደሰው ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ እንደቀድሞ ሁሉ በቀጣይም የሚጠበቅባቸውን እንደሚያበረክቱ የገለጹት ደግም አቶ አበራ መንግሥቱ ናቸው።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የባሌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም ኃይሌ፤ የዞኑ ነዋሪዎች ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ውጤታማነት በቦንድ ግዥና በስጦታ በርካታ ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

አሁንም ግድቡ እስከሚመረቅ ድረስ ሕብረተሰቡ፣ የፀጥታ አካላት እና ባለሃብቶች ተሳትፏቸውን እንዲያስቀጥሉ የንቅናቄ ስራዎች እንደሚጠናከሩ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ላይ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በቅርቡ ለምረቃ እንደሚበቃ መግለጻቸው ይታወሳል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026