
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2017(ኢዜአ)፦ ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት 162 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።
ገቢው የተገኘው ከድምጽ ጥሪ፣ ከኢንተርኔት አገልግሎት፣ ከቫስ፣ ከመሠረተ ልማት ማጋራት፣ ከቴሌኮም ቁሳቁስ ሽያጭና ከሌሎች ምንጮች መሆኑንም ገልጿል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፥ የኩባንያውን የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምና መሪ የሶስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ማጠቃለያ ሪፖርት ለመገናኛ ብዙኃን ይፋ አድርገዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ከሶስት ዓመት በፊት የቴሌኮም እና የዲጂታል አገልግሎትን ማሳደግ የሚያስችል መሪ የሶስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውሰዋል።
ኩባንያው ከቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር በዲጂታላይዜሽን በኩል አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አመላክተዋል።
የቴሌኮም አገልግሎት አሰጣጡን ከማስፋትና ጥራቱን ከማሳደግ አኳያ ከፍተኛ እድገት መመዝገቡንም ነው ዋና ስራ አስፈጻሚዋ የገለጹት።
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረትም ትርጉም ያለው ስራ መሠራቱን አንስተዋል።
በመሪ የሶስት ዓመት የእድገት ስትራቴጂ ደግሞ 26 ከተሞችን በ5ጂ ኔት ወርክ እንዲሁም 936 ከተሞችን በ4ጂ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በዚህም በመላ ሀገሪቱ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን የፈጣን ኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ምህዳር መፈጠሩን ተናግረዋል።
በ2017 በጀት ዓመት 1ሺህ 683 አዳዲስ የሞባይል ጣቢያዎች መገንባታቸውንም ነው የጠቀሱት።
በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ10ሺህ በላይ የሞባይል ጣቢያዎች ተተክለው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙም አመላክተዋል።
በበጀት ዓመቱ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፥ 162 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026