🔇Unmute
አዲስ አበባ፤መስከረም 30/2018(ኢዜአ)፦በክልሎቹ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡና ብልፅግናን እውን በሚያደርጉ የልማት ሥራዎች አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መምጣቱን የጋምቤላና ሲዳማ ክልሎች ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮች ገለፁ።
የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጋትሉዋክ ሮን በክልሉ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ለሚፈልጉ አካላት በርካታ አማራጮች መኖራቸውን ተናግረዋል።
በማዕድን ዘርፍ የሚታየውን ህገወጥ ተግባር በመቆጣጠርና ፍትሃዊ አሰራር በማስፈን ከክልሉ አልፎ እንደአገር የተሻለ ገቢ ማግኘት እንደሚቻል ገልፀዋል።
በክልሉ ለግብርና ምቹ የሆነ ሰፊ መሬት፣ የቁም እንስሳትና የዓሳ ሀብት በመኖሩ ያለውን ሀብት በመጠቀም፣ የግብይት ስርዓቱን በማሳለጥና የአገር ውስጥና ቀጣናዊ የንግድ ትስስርን በማጠናከር ገቢን ማሻሻል ይቻላል ብለዋል።
በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው በተለይም በሆቴል ልማት፣ መሬት አስተዳደርና ህገ ወጥ ኬላ ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመቆጣጠር በክልሉ የሚሰበሰበውን ገቢ ለማሳደግ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያ ከተረጂነት ለመውጣት የጀመረችውን ጉዞ ለማሳካት በክልሉ የተጀመረውን ልማት በማጠናከር የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልፀዋል።
የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ በየነ በራሳ በበኩላቸው፤ ክልሉ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በትምህርት ለትውልድ መርሃ ግብር በላቀ የህዝብ ተሳትፎ የትምህርት ቤቶች ገፅታ እየተቀየረ መምጣቱን አስታውቀዋል።
በጤና፣በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርና በእርሻ ልማት አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መከናወናቸውን ጠቁመው፥ የግለሰቦችን ህይወት ለመቀየር የቤተሰብ ብልፅግና (አቴቴ ጅሬኛ) የተሰኘ መርሃ ግብር እየተተገበረ መሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል።
በዚህም የክልሉን ሀብት በመጠቀም የክልሉን ብሎም የአገርን ብልፅግና እውን ለማድረግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮቹ በክልላቸው በተያዘው ዓመት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልፀው፤ ይህንንም ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የገቢ ዘርፍ ሪፎርም የሀገር ብሎም የክልሎች የገቢ አሰባሰብ አፈፃፀም እድገት ለማስመዝገብ ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡
በዘርፉ ያሉ ችግሮችን በቅንጅት በመፍታት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026