የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

ሕገ ወጥ ድርጊት ሲፈጽሙ በተገኙ የነዳጅ ማደያዎች ላይ ርምጃ ተወሰደ

Oct 23, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 12/2018 (ኢዜአ)፡- በ2018 የበጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከነዳጅ ሽያጭ እና ማከፋፈል ሂደት ጋር በተያያዘ ሕገ ወጥ ድርጊት በፈጸሙ ማደያዎች ላይ ርምጃ መወሰዱን የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን አስታወቀ።

በዚህም መሠረት፤ ዲጂታል ሽያጫቸው ከ50 በመቶ በታች በሆኑ 354 የነዳጅ ማደያዎች ላይ በአዋጁ መሠረት ርምጃ መወሰዱን የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ በቀለች ኩማ ለኢዜአ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ዲጂታል ሽያጫቸው ዝቅተኛ በሆኑ ሥድስት የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ላይ በአዋጁ መሠረት ለሁለት ወራት የነዳጅ ጭነት እንዳይደረግላቸው መደረጉንም ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል የዲጂታል ሽያጫቸው መጠነኛ በሆኑ ሰባት ኩባንያዎች ላይ በአዋጁ መሰረት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ነው የጠቀሱት።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አንድ ማደያ ነዳጅ በበርሜል በመቅዳት የጥቁር ገበያ ሽያጭ ለማከናወን ሲንቀሳቀስ በመያዙ ለሥድስት ወራት ከነዳጅ ትስስር መታገዱንም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል መዳረሻው አዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ በሚገኝ ማደያ የነበረ አውቶ ቦቴ መዳረሻውን በመቀየር ወደ ሌላ ከተማ በመጓዙ ለሥድስት ወራት ከነዳጅ ትስስር እንዲታገድ መደረጉን ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በዲላ ከተማ የሚገኝ አንድ ማደያም መንግሥት ካወጣው ዋጋ በላይ በመሸጡ የነዳጅ አቅርቦት እንዳያገኝ በሲስተም ሎክ መደረጉን ነው ያረጋገጡት።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የነዳጅ አቅርቦት፣ ሥርጭትና ግብይት ቁጥጥር ሥርዓቱ ፈጣን፣ አስተማማኝና ጥራት ያለው እንዲሆን በቴክኖሎጂ የታገዙ አሠራሮችን ማጠናከሩንም አስታውቋል።

ሁሉም የነዳጅ አከፋፋዮችና ማደያዎች ህግን ተከትለው መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026