🔇Unmute
ዲላ፤ ጥቅምት 20/2018(ኢዜአ)፦ የባህር በር ጥያቄን ማንሳት እንደ ጥፋት ይቆጠር የነበረበት ጊዜ አብቅቶ አሁን የመብት ጥያቄ መነሳቱ ተገቢና ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዳይ መሆኑን ምሁራን ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በቅርቡ ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ህጋዊ፣ ታሪካዊና መልክዓ ምድራዊ መብት የነበራት ብትሆንም ለምን እና በማን ውሳኔ እንዳጣች እስካሁን መረጃና ማስረጃ ማግኘት አለመቻሉን መግለጻቸው ይታወሳል።
በመሆኑም ከባህር ልትገለልና የባህር በር ልታጣ አይገባም በማለት መንግስት የባህር በር ጉዳይን የህልውና ጉዳይ አድርጎ ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የታሪክ መምህርና ተመራማሪ ፕሮፌሰር አየለ በክሪ እና በአውስትራሊያ የናሽናል ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ዳንኤል መኮንን፤ የባህር በር ጥያቄን ማንሳት እንደ ጥፋት ይቆጠር የነበረበት ጊዜ አብቅቶ የመብት ጥያቄ መነሳቱ ተገቢና ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዳይ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ ባህር አካሏ የባህር በር ደግሞ የእድገትና ህልውናዋ መሰረት እንደነበር የሚያስታውሱት ፕሮፌሰር አየለ በክሪ፤ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በመንፈግ የባህር በር ለምን አጣች የሚለው ጉዳይ ዜጎችን እያስቆጨ ያለ መሆኑን አንስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ቀይ ባህር ላይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ መብት ያላት መሆኑን መግለፃቸው ተገቢና ትክክለኛ ነው ብለዋል።
ከዚህ በፊት የባህር በር ጥያቄን ማንሳት እንደ ጥፋት ይቆጠር የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በቁጭት መንግስት የሀገር የህልውና ጉዳይ አድርጎ መያዙን አድንቀው የኢትዮጵያ ህጋዊ፣ ታሪካዊና መልክዓ ምድራዊ የባህር በር ባለቤትነት መብቷ ምላሽ ሊያገኝ እንደሚገባ በአጽንኦት ሰጥተዋል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስት ጥረት እንዳለ ሆኖ ከቀይ ባህር በቅርብ ርቀት ላይ ሆነን በተዘጋ ሀገር ውስጥ መኖር የሌለብን በመሆኑ ሁላችንም ለመብትና ተጠቃሚነታችን በጋራ መቆም አለብን ብለዋል።
በአውስትራሊያ ናሽናል ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ዳንኤል መኮንን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ መንግስት የያዘው ጠንካራ አቋም የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ፣ ካላት የህዝብ ቁጥር እና ግዙፍ የኢኮኖሚ ዕድገት አንፃር የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ያለበት ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልክዓ ምድራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ መሆኑ ማንሳታቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት ምክንያትም በማን እንደተወሰነ የሚያመላክት አንዳችም ማስረጃ እንደሌለ ጨምረው ማስረዳታቸው እንዲሁ።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026