የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤን በመለወጥ የተሟላ ብልጽግና ማረጋገጥን ያለመ ነው -የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Nov 3, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2018(ኢዜአ)፦ የገጠር ኮሪደር ልማት የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤን በመለወጥ የተሟላ ብልጽግና ማረጋገጥን ያለመ መሆኑን የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል፦

መንግሥት ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማን ለመገንባት የኮሪደር ልማቱን ከአዲስ አበባ በመጀመር ሁሉም ክልሎች ላይ ከተሞችን የማልማት ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህ የኮሪደር ልማቱ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ከማረጋገጥ አኴያ የጎላ ሚና አለዉ፡፡ ሌሎች ከተሞችም አዲስ አበባ ከኮሪደር ልማት በፊት ምን እንደምትመስል፤ ልማቱ ሲሰራ የነበረዉን ሁኔታ እና የኮሪደር ልማቱ ካለቀ በኃላ ያለዉን ለዉጥ የሚያሳይ ልምድ ከወሰዱ በኃለ በመላዉ ኢትዮጵያ 68 ከተሞች ላይ የኮሪደር ልምት መስራት ተችሏል፡፡

የኮሪደር ልማቱ ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሳሳረ ልማት ሲሆን፤ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሓዊ ልማት ለዜጎቻችን ለማቅረብ በማለም ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ ሊሆን በሚችል መልኩ ከተሞች እያለሙ ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚኖረዉ ገጠር በማሆኑ የዜጎችን ህይወት ለመቀየር እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በከተማ የተሰራ የኮሪደር ልማት በቂ አይደለም፡፡ በከተሞች የታየዉን አመርቂ ዉጤት በገጠርም መታየት አለበት።

ስለዚህ የኮሪደር ልማቱ በከተማ ብቻ ሳይገደብ የገጠሩን ማህበረሰብ አኗኗርን ለማሻሻል የገጠር ኮሪደር ልማት ተግባራዊ ተደርጓል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2017 ግንቦት ወር መጨረሻ የገጠር ኮሪደር ልማት አካል የሆነውን ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ ማስጀመራቸው ይታወሳል። የተሻላ ኖሮን ፍለጋ ከከተማ ወደ ገጠር የሚደረገዉን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገትን ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ ነዉ፡፡ ይህ ደግሞ የተስተካከለ ኑሮን እና ከተሜነትን ወደ ገጠር በማምጣት፤ ሞዴል የገጠር መንደሮቹ ቀላል ወጪ የሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ፤ እንዲሁም አርሶ አደሩ ጤናማ እና ክብር ያለውን ህይወት እንዲኖር የሚያስችል የልማት አካል ነዉ። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ስነ ምህዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ሲሆን ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው።

ከለዉጡ በፊት የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነው የገጠሩ አካባቢ ትኩረት ተነፍጎት የቆያ ሲሆን፤ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ ወደ ከተማ የሚሄደውን አርሶ አደር በሚኖርበት ተረጋግቶ እሴት መጨመር ላይ እየሰራ እንዲኖር የሚያስችል ሁኔታ ነዉ የለውጡ መንግሥት የፈጠረዉ። የገጠር ኮሪደር አጠቃላይ የኅብረተሰብ ሽግግርን የሚያመጣ እና መሰረተ ልማትን ጨምሮ የተለያዩ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ጉዳዮችን ያቀፈ ሲሆን፤ በገጠር አካባቢዎች ዘመናዊ አኗኗርን የሚፈጥር እና የአርሶ አደሩን ህይወት የሚቀይር ይሆናል።

በአጠቃላይ የገጠር ኮሪደር ልማት አርሶ አደሩ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚና ዘመናዊ ስልተ-ምርት እንዲከተል የምየደርግ ሲሆን አርሶ አደሩ ባህሉንና ወጉን ጠብቆ አካባቢውን ንጹህ፣ ጓሮውን በዶሮ፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ እንዲሁም በማርና ወተት ምርት የተትረፈረፈ በማድረግ ቀላል የአኗኗር ስልት እንዲከተል ያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026