🔇Unmute
ወላይታ ስዶ፤ ጥቅምት 27/2018(ኢዜአ)፦ በወላይታ ሶዶ ከተማ መናኸሪያ የተጀመረው በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ከእንግልት እና አግባብ ካልሆነ የታሪፍ ክፍያ ታድጎናል ሲሉ የመናኸሪያው ተገልጋዮች ተናገሩ።
በወላይታ ሶዶ ከተማ የተጀመረው የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት ዙሪያ ኢዜአ ተገልጋዮችን አነጋግሯል።
ተገልጋዮቹ እንዳሉት፤ በከተማዋ መናኸሪያ የተጀመረው በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር ከዚህ ቀደም ይገጥማቸው የነበረን ከታሪፍ በላይ የመክፈልና አላስፈላጊ እንግልት አስቀርቶላቸዋል።
አቶ ብሩክ ዘውዴ ከዚህ ቀደም የትራንስፖርት አገልግሎቱ ካለመዘመኑ የተነሳ ለተለያዩ ችግሮች ይዳረጉ እንደነበር አስታውሰዋል።
በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት ከተጀመረ ወዲህ ያለአግባብ ይደርስብን የነበረው እንግልትና የታሪፍ በላይ ክፍያ ከማስቀረት ባሻገር ጊዜያችንን ቆጥቦልናል ብለዋል።
ሌላኛዋ ተገልጋይ ወይዘሮ የእናትፋንታ ኢያሱ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ትክክለኛውን ታሪፍ እንኳን ለማወቅ ይቸገሩ እንደነበር አስታውሰው የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት በርካታ መረጃዎችን መዝግቦ በመያዙ ሳይጨናነቁ እና ትርፍ ሳይከፍሉ መገልገል መጀመራቸውን ገልጸዋል።
ተሽከርካሪዎችም ትርፍ መጫን ስለማይችሉ እና ወጪ ወራጅ ስለማይበዛ ወዳሰብንበት ቦታ በጊዜ እንድንደርስ ከማድረጉ በተጨማሪ የትራፊክ አደጋም እንዲቀንስ ስለሚያግዝ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ተናግረዋል።
ባለፉት ዓመታት በማህበራትና በአሽከርካሪዎች ይሁንታ ላይ ተመስርቶ የቆየው የትራንስፖርት አገልግሎት ተሳፋሪዎችን ለችግር ዳርጓቸው መቆየቱን የተናገሩት ደግሞ የወላይታ ሶዶ ከተማ መናኸሪያ ኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ አቶ ኢያሱ ካፒቴን ናቸው።

ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ታስቦ ወደ ኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት ከተገባ ሁለት ወራት ማለፉን ጠቁመው ይህ አገልግሎት ከተጀመረ ወዲህ ተሳፋሪዎች ያነሱት የነበረው ከታሪፍ በላይ ክፍያና መጉላላት ቀንሶ ለህዝቡ እፎይታ መስጠቱን ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ ምክትልና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ ብርሃኑ ጌቦ (ዶ/ር) እንደገለጹት በወላይታ ሶዶ እና ሳውላ ከተሞች መናኸሪያዎች የተጀመረው የኢ-ቲኬቲንግ አገልግሎት የትራፊክ ፍሰቱን በማሳለጥ ከእንግልት የፀዳ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት አስችሏል።

በሁለቱ መናኸሪያዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሻለ ለውጥ መመልከት ችለናል ያሉት ኃላፊው አገልግሎቱ ህገወጥ የታሪፍ ክፍያን እና የተሳፋሪዎችን ጊዜ በመቆጠብ የትራፊክ ፍሰቱን ማሳለጡን ተናግረዋል።
በመሆኑም በክልሉ 12 ዞኖች ዋና ዋና ከተሞች አገልግሎቱን ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አንስተዋል።
ሁሉም ተሳፋሪዎች ኢ-ቲኬት ይዘው እንዲወጡ መደረጉ የግል ጥቅማቸውን ያስቀረባቸው የተሽከርካሪ ማህበራት የሚፈጥሩትን ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በመሆኑም የትራንስፖርት አገልግሎት ችግሮችን ለመቅረፍና የተገልጋዩን ማህበረሰብ እርካታ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንደሚያስፈልግም ኃላፊው ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026