የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

ወጣቶች የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ ውጤታማ ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል

Nov 13, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ህዳር 1/2018 (ኢዜአ)፦ወጣቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ ውጤታማ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚጠበቅባቸው የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ ገለፁ።

ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚካሔደው 10ኛው አገር አቀፍ የወጣቶች የፈጠራ ስራ ውድድር የማስጀመሪያ መረሃ-ግብር ተካሒዷል።

የውድድር መረሃ ግብሩን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ አየለች እሸቴ እንደገለጹት፤ መንግስት ዲጂታል ኢትዮጵያ በሚል መርህ ለሳይንስ፣ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው።


በተለይም የቴክኖሎጂ ዘርፉ በአገር ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ ያለውን አስተዋጽኦ ለማጉላት በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል።

ለአብነትም የዘርፉን የአሰራር ስርዓት ማሻሻል የሚያስችሉ የፖሊሲና የሪፎርም ስራዎች በዋናነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በዚህም ባለፉት የለውጥ ዓመታት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና ከአጋር አካላት ጋር በትብብር የሚዘጋጀው የፈጠራ ስራ ውድድር አንዱ ማሳያ ተደርጎ እንደሚወሰድ አብራርተዋል።


በዚህ ውድድር የሚወጡ የፈጠራ ስራዎች ወጣቶች በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸው እውቀትና አቅም ከፍ እያለ መምጣቱን በተግባር የሚያሳይ ስለመሆኑም ሚኒስትር ዴኤታዋ አክለው ገልፀዋል።

ወጣቶች የማህበረሰቡን ችግር የሚያቃልሉ የፈጠራ ስራዎችን በማበልፀግ በዘርፉ የሚኖረውን ተወዳዳሪነት ከፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተወካይ ሰላምይሁን አደፍርስ በበኩላቸው፤ ተቋሙ ቴክኖሎጂያዊ አሰራሮች እንዲሰፉ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህ ረገድ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል በቅርቡ የጸደቀው የስታርት አፕ አዋጅ አንዱ ሲሆን፤ ይህም የፈጠራ ውጤቶች እንዲበረታቱና ከሃሳብ ወደ ተግባር እንዲሸጋገሩ እድል ፈጥሯል።


በዚህ ውድድር ላይ የሚቀርቡ የፈጠራ ስራዎች በዘርፉ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂያዊ አሰራሮች እውን እንዲሆኑ ከማስቻል ባሻገር እይታንና አመለካከትን ለማስፋት ዓይነተኛ ሚና አላቸው ብለዋል።

ዲጂታል ኢትዮጵያን ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ከተቋማት ጋር የሚሰሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል ነው ያሉት።


የስቴም ፓውር የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስሜነው ቀስቅስ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ተቋሙ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ወጣቶች በግብዓት በእውቀትና በፋይናንስ መደገፍ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነው ብለዋል።

በተከታታይ ሲካሔድ በቆየው በዚህ ውድድር ላይም በአጋርነት በመሳተፍ ተወዳዳሪዎቹ ሃሳባቸው ተግባራዊ እንዲሆን የሚጠበቅበትን ሃላፊነት ሲወጣ መቆየቱን ገልጸዋል።

ይህም እንደ ሀገር ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ብሎም የፈጠራ ስራን ለማበረታታት የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ ስለመሆኑ ነው የገለጹት።

ተወዳዳሪዎች የፈጠራ ሃሳባቸው እንዲያሸንፍና ተሸላሚ እንዲሆን ከማድረግ ባለፈ ለማህበረሰቡ ብሎም ለአገር ጠቃሚ የሆኑ ስራዎችን እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የውድድሩ ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው፤ ውድድሩ ስራዎቻቸውን ለማስተዋወቅና ተጨማሪ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ እንደሚያግዛቸው ጠቁመዋል።

የሮቦት ቴክኖሎጂን በመስራት ለውድድር የቀረበው ወጣት ሙአዝ በክሩ፤ በአሁኑ ወቅት በቴክኖሎጂ ዘርፍ የተፈጠረውን እድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብሏል።


በቀጣይ በሮቦት ቴክኖሎጂ ዘርፍ የኢትዮጵያን ተወዳዳሪነት ከፍ የማድረግ ህልም እንዳለው ጠቁሞ፤ ለዚህም ከወዲሁ የሚጠበቅበትን ጥረት እያደረገ ስለመሆኑ ነው የገለጸው።

ውሃን ከብክለት መከላከል የሚያስችል የፈጠራ ስራ ይዛ የቀረበችው ወጣት አቢጊያ መንግስቱ በበኩሏ፤ የህክምናና የኢንጅነሪንግ እውቀትን በማጣመር የሰራችው የፈጠራ ስራ መሆኑን ገልጻለች።


በተሰማራችበት ሙያ የአገሯን እድገት ማፋጠን የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን ማበልጸግ እንደምትፈልግ ጠቁማ፤ ለዚህም ''ይህ ውድድር ጥሩ ልምድ የማገኝበት ነው'' ብላለች።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ ነው</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የቁልፍ መሰረተ ልማቶች ጥበቃ አዋጅን ሥራ ላይ ለማዋል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስ...

Feb 28, 2025

<p>በዞኑ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ ነው</p>

ደሴ፤ የካቲት 16/2017 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ወሎ ዞን በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ መኮንን ገለ...

Feb 24, 2025

<p>የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተደረገ ነው - ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል</p>

አሶሳ ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ):- የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ችግር ፈቺ ስራዎችን እንዲያከናውኑ እየተሰራ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገ...

Feb 24, 2025

<p>ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው -የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ቀንድ የልማት ትስስርና የኢኮኖሚ ውህደት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ የአፍሪካ ቀንድ...

Feb 12, 2025