🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያከናወናቸውን ሃምሳ ስድስት የምርምር ውጤቶች በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ተደራሽ ማድረጉን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት በ2013 ዓ.ም ከተመሰረተ ጀምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት አመርቂ እድገት አስመዝግቧል፡፡
በዘርፉ የወጣቶች ግንዛቤና ተሳትፎ እንዲጠናከር የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በፍጥነት እያደገ የሚገኘው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፈ ብዙ እድሎችና ጠቀሜታዎችን እያስገኘ ቢሆንም በአንፃሩ ለመረጃ ምንተፋም የተጋለጠ መሆኑ ይታወቃል።

በዚህ ረገድ በዘርፉ የሚከናወኑ ምርምሮች የአንድ ሀገር ወይም ተቋም የወደፊት እድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ ናቸው።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን እያስገኘ ያለው ውጤት ለዚህ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በማደራጀት ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር ተችሏል፡፡
በዚህም ተቋሙ ተወዳዳሪ የሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ለአብነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ 56 የምርምር ውጤቶችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ማሳተሙን አንስተዋል።
ከምርምር ውጤቶቹ መካከል ዘጠኙ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ እንዳገኙ ጠቅሰው፤ ይህ ስኬት በሌሎች የምርምር ውጤቶችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ኢንጂነር ወርቁ (ዶ/ር) በርካታ ሀገራት በጤና፣ በግብርና እና በአገልግሎት ዘርፎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምርታማነትን በእጥፍ በማሳደግ እና አገልግሎት አሰጣጣቸውን በማዘመን ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
በመሆኑም በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ የሀገሪቷና የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ፣ በትውልድ ላይ መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘርፉ ያለው የወጣቶች ግንዛቤና ተሳትፎ እንዲጠናከር የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት 200 ጀማሪ የፈጠራ ባለሙያዎች በኢንስቲትዩቱ የስታርት አፕ ፕሮግራም ተካተው እየሰሩ እንደሚገኙ ጨምረው አስታውቀዋል።
ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በዘርፉ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ የሰለጠነ በቂ የሰው ሃይል ለማፍራት የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።
'ኢንተሊጀንስ ለሁሉም' በሚል መሪ ሀሳብ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በሁሉም ዘርፎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026