🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 21/2018 (ኢዜአ)፡-የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያውቁና በዲጂታል ዘርፍ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ መሠረት እንደጣለላቸው ወጣቶች ገለጹ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የተደረገው የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶች በኦንላይን የኮዲንግ ስልጠና የሚወስዱበት ሂደት ነው፡፡
በኢትዮጵያ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ ስታርትአፖች በሀገሪቱ ፈጣን ዕድገት ለማምጣት እና ገበያውን ለመለወጥ የተያዘውን ጥረት በእጅጉ እያገዙ ይገኛሉ፡፡
ይህን ተከትሎ በርካታ ስታርታፖች በቴክኖሎጂ በመታገዝ በሚሰሯቸው ስራዎች የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ የግብርና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የሎጂስቲክስና የኢ-ኮሜርስ ዘርፎች በስፋት ተደራሽ እንዲሆኑ እያስቻሉ ነው፡፡
ኢዜአ ያነጋገራቸው ስታርታፖች ኢኒሼቲቩ የዲጂታል አቅማቸውን በማጎልበት ተጨማሪ ክህሎት እንዲጨብጡ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ ኤ አይ ድርጅት መስራች ወጣት ቃልኪዳን ደምሌ፤ በቴክኖሎጂው ዘርፍ በመሰማራት ውጤታማ ስራዎችን ለማበርከት የወሰደችው የኮደርስ ስልጠና በሚገባ እንደጠቀማት ተናግራለች፡፡
በሁለት የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች የሚሰራ መተግበሪያ በመፍጠር ወደ ስራ ማስገባት መቻሏን የምትናገረው ወጣቷ ለዚህ ስኬትም ስልጠናውን መውሰዷ እንደረዳት ገልጻለች፡፡
ስልጠናው በተለይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳደሪ ለመሆን፣ ፈጠራን ለማላቅ ብሎም የሥራ ዕድሎችን ለማግኘት እንዳስቻላት ጠቅሳለች፡፡
ያሬድ እንዳለ በበኩሉ መንግስት እያደረገላቸው በሚገኘው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ከራሳቸው አልፈው ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻላቸውን ተናግሯል፡፡
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ወጣቶች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንዲያውቁና በዲጂታል ዘርፍ ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ መሠረት መጣሉን ጠቅሷል፡፡
ይህም ስታርታፖች በቴክኖሎጂው ዘርፍ ራሳቸውንና ሀገራቸውን የሚለውጡ የፈጠራ ስራዎችን እንዲያበረክቱ ዕድል መፍጠሩን ተናግሯል፡፡
የፌዶ ፓወር ሶሉሽን ድርጅት ባለቤት ወጣት ፌደሳ ሹማ በበኩሉ በፈጠራ ውጤቱ በመታገዝ ችግር ፈቺ ስራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡
የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስራው ለማሳደግ የሚረዳውን ተጨማሪ ዕውቀት በማስጨበጥ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን እንዳስቻለው ገልጿል፡፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026