🔇Unmute
አምቦ፤ ሕዳር 23/2018 (ኢዜአ)፦በአምቦ ከተማ በከተማ ግብርና የተሰማሩ ነዋሪዎች ከምግብ ፍጆታ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናገሩ።
በአምቦ ከተማ በከተማ ግብርና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት የተሰማሩ ነዋሪዎች በልማቱ የተመጣጠነ ምግብን ለቤተሰባቸው ከማቅረብ ባለፈ ተጨማሪ ገቢ በማግኘት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መሆኑን ተናግረዋል።

በዘርፉ ከተሰማሩ መካከል አርሶ አደር ዘርይሁን አያልቅበት፤ ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት በአነስተኛ መሬታቸው ላይ ቲማቲም በማልማት ከቤተሰብ ፍጆታ አልፈው ለገበያ በማቅረብ ተጨማሪ ገቢ አግኝተዋል።

ለገበያ ከሚያቀርቡት አትክልት ሽያጭ በመቆጠብ የወተት ላም መግዛታቸውንም ተናግረዋል።
የአትክልት ልማቱን ውጤት በየጊዜው በማየታቸው አሁን ላይ ስራውን በማስፋት ቀይ ሽንኩርትና ሌሎች የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እያለሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሌላው በከተማ ግብርና የተሰማሩት አቶ ዘገየ አከዋቅ በበኩላቸው፥ ወደ አትክልት ልማት ከመግባታቸው በፊት ብዙም ተጠቃሚ እንዳልነበሩ አስረድተዋል።

ከግብርና ባለሙያዎች ያገኙትን ድጋፍ ተጠቅመው በከተማ ግብርና በመሰማራት የአመጋገብ ስርዓታቸውን ለማሻሻል እና ገቢያቸውን ለማሳደግ እየተጉ ነው።
በዚህም ድንች እና ነጭ ሽንኩርት በማልማት ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
የአምቦ ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ታከለ ኩምሳ እንዳሉት፤ በአምቦ ከተማ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አካል የሆነው የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ለምግብ ዋስትናና ለስራ እድል ፈጠራ እያገዘ ነው፡፡

በከተማው የበጋ መስኖ ልማት በአትክልትና ፍራፍሬ ለማልማት ከታቀደው 95 ሄክታር መሬት ውስጥ እስከ አሁን 36 ሄክታር መሬት በተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬ መሽፈኑን ተናግረዋል፡፡
የከተማው ነዋሪዎች በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በመሳተፍ አትክልትና ፍራፍሬ በማምረት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙና ገቢያቸውን እንዲያሳድጉ ድጋፍና ክትትል መደረጉን አንስተዋል።
ምርታማነታቸውን ለማሳደግ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ ግብአት በማቅረብ ለገበያ ማረጋጋት ጭምር እያገዙ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026