የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በኦሮሚያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የማስፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው

Dec 8, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 28/2018 (ኢዜአ)፡-በኦሮሚያ ክልል በ5 ከተሞች የተጀመረውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማስፋት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ዳመጠው ገመቹ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርምን በሙሉ አቅም ተግባራዊ ለማድረግ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በዚህ መሰረት ክልሉ ለሪፎርሙ ተግባራዊነት ያለውን ምቹ ሁኔታዎችን በመጠቀም የሚያስፈልጉ ሰነዶችን በማሟላት የዝግጅት ምዕራፍ አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።

በተለይም ሪፎርሙ በክልሉ በፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ፣ በጤና ቢሮ፣ በትምህርት ቢሮ፣ በገንዘብ ቢሮና በአጠቃላይ በ5 የመንግስት መስሪያ ቤቶች በቀጣይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም አንስተዋል።

ከነዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንዱ ሲሆን የክልሉን ህዝብ ከእንግልትና ካልተገባ ወጪ በማዳን ፈጣን፤ ቀልጣፋና ግልጽነት ያለው የተሻለ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።


ሪፎርሙን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ የሰው ሀይል ማሰልጠን ፣ መሰረተ ልማቶችን ማሟላት፣ ቴክኖሎጂዎቹን ማበልጸግና ግንባታዎችን ማስፋትና ለተገልጋዩ የግንዛቤ ፈጠራ መስጠት ከሚተገበሩት ዋና ዋና ተግባራት መካከል መሆናቸውን አቶ ዳምጠው ገልጸዋል።

በዚህ መሰረት በ2018 በጀት አመት በአንደኛ ዙር በሸገር፤ በቢሾፍቱ፤ በአዳማ፤ በሻሸመኔና ጅማ ከተሞች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩን አስታውቀዋል።

አገልግሎቱ ከተጀመረ ወዲህ ባለፉት 3 ወራት 180 ሺህ ዜጎች አገልግሎቱን በማግኘት የእርካታ መጠናቸው ከ95 በመቶ በላይ መሆኑን በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መለየቱን አንስተዋል።


በክልሉ በበጀት አመቱ አገልግሎቱን አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ ከሸገር ከተማ ባሻገር በ13 ትልልቅ ከተሞች ስራው ተጠናቆ አገልግሎት እንደሚሰጥ አብራርተዋል።

በዚህም በሻኪሶ፣ ሞያሌ፣ ሸኖ፣ ነጆና ዶዶላ ከተሞች እንዲሁም በሁለቱ የአርሲ ዞኖች፤ በጅማ፣ በምስራቅ ሀረርጌና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች አገልግሎቱ ተደራሽ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

በዘንደሮ አመት በኦሮሚያ ክልል በአጠቃላይ በከንቲባ ደረጃ በሚተዳደሩት በ52 ከተሞች በተሟላ መልኩ አገልግሎቱን ለማስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ አንስተው በቀጣይ እስከ ቀበሌዎች ድረስ ስራው የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026