🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 30/2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራሟን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ስታንዳርድና መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ እንደምትተገብር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኑክሌር ኢነርጂ ዲፓርትመንት ኃላፊ ሜካኤል ቹዳኮቭ (ዶ/ር) ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጋር ትብብርን በሚያጠናክሩ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት መደረጉን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኃይልና ቴክኖሎጂን ለንጹህ ኢነርጂ፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪና ለምርምር ልህቀት የመጠቀም ጽኑ መሻት እንዳላት አመልክተዋል።
ለዚህም ሀገራዊ የኑክሌር ኃይል ፕሮግራምን በቅርቡ መጀመሯንና የኑክሌር ኃይል ኮሚሽንን በማቋቋምም በይፋ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራሟን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ስታንዳርድና መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ እንደምትተገብርም አረጋገጠዋል።
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ኢትዮጵያ ከኑክሌር ኃይል ስትራቴጂካዊ ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ የጀመረችውን ጉዞ እውን ለማድረግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለጹላቸውም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026