የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ የኃይል ምርት እና አጠቃቀም ስርዓት ለቀጣናው እና ለአፍሪካ መትረፍን አላማ ያደረገ ነው

Dec 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ታህሳስ 1/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የኃይል አመራረት፣ ስርጭት እና አጠቃቀም ስርዓቷን ከሀገር አልፎ ለቀጣናው እና ለአፍሪካ መትረፍን አላማ በማድረግ እየሰራች እንደምትገኝ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

የአፍሪካ ሕብረት ያዘጋጀው የአፍሪካ የኃይል አጠቃቀም ውጤታማነት ኮንፈረንስ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ኮንፍረንሱን በጋራ ከፍተዋል።

የአፍሪካ ህብረት ያዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የኃይል አጠቃቀም ውጤታማነት ኮንፍረንስ (Energy Efficiency Conference) በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ዛሬ ተጀምሯል።


ኮንፍረንሱ እ.አ.አ በ2024 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 29ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) ይፋ የተደረገው የአፍሪካ ኢነርጂ ውጤታማነት ጥምረት ማዕቀፍ ስር የሚካሄድ ነው።

“የአፍሪካ የኢነርጂ ውጤታማነት አጀንዳን በስትራቴጂካዊ አጋርነት ውጤታማ ማድረግ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው።

አህጉራዊው ሁነት የተዘጋጀው የአፍሪካ ህብረት ልዩ ተቋም በሆነው የአፍሪካ ኢነርጂ ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ መንግስት ትብብር ነው።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያ ለአህጉራዊ የኃይል አመራረትና አጠቃቀም ስኬታማነት እያደረገች ስለምትገኘው ጥረት ተሞክሮ ማካፈሏን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የኃይል አመራረት፣ ስርጭት እና አጠቃቀም ስርዓት ለታዳሽ የኃይል አማራጮች ቅድሚያን የሚሰጥ፣ ኢነርጂን በማምረት ሂደት ሊፈጠር የሚችል የአየር ንብረት ተፅእኖን ከግንዛቤ ውስጥ ያስገባ መሆኑን አመልክተዋል።


እንዲሁም መሰረቱን በጋራ ተጠቃሚነት ላይ አድርጎ ለአህጉራዊ ትስስር እና ዘላቂ ልማት ከፍተኛ አስተዋዕፆ ማበርከትና ለጎረቤት ሀገራት ጭምር መትረፍን ግቡ አድርጎ ተግባራዊ የሚደረግ እንደሆነም ተናግረዋል።

በበርካታ የኃይል አማራጮች የተሞላችው አፍሪካም የኃይል ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በተሰናሰለ ሁኔታ አካባቢያዊ ስነምህዳርን ከግንዛቤ ውስጥ ባስገባ መልኩ ኃይልን ማመንጨት ይገባል ነው ያሉት።

የተመረተውን ኃይል በውጤታማነት ማሰራጨትና መጠቀም እኛ አፍሪካዊያን በቀጣይ ትኩረት ሰጥተን በትብብር ልንሰራውና ልምድ ልንለዋወጥበት የሚገባ ወሳኝ ጉዳይ ነው ብለዋል አቶ አደም።

ኮንፍረንሱ የኢነርጂ ውጤማነትን በማረጋገጥ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፣ ዘላቂ ልማት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የተግባር ምላሽ አቀጣጣይ ሞተር የማድረግ አላማ ያለው መሆኑ ተገልጿል።

የመጀመሪያው የአፍሪካ ኃይል አጠቃቀም ውጤታማነት ኮንፍረንስ እስከ ነገ ይቆያል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ ቀርቧል  

ጅማ፤ ሚያዝያ 16/2018 (ኢዜአ)፡- በጅማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 52 ሺህ ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ተናገሩ...

Apr 24, 2026

የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂ የማጠናከር ተግባራት እየተከናወነ ነው

ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መ...

Apr 22, 2026

ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካውያን በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...

Apr 15, 2026

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026