🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥር 24/2018 (ኢዜአ)፡- በአፍሪካ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ ሁሉም ሀገራት ለውኃ አቅርቦት፣ ለጥራት እና ለንጽህና መሰረተ ልማቶች ቅድሚያ መስጠት እንዳለባቸው የአፍሪካ ሕብረት አስገነዘበ።
በሕብረቱ የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚ እና የዘላቂ አካባቢ ጥበቃ ኮሚሽነር ሙሴ ቪላካቲ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ አህጉራዊው የግብርና ልማት ፕሮግራም ባለፉት 20 ዓመታት በአባል ሀገራት ዘንድ ጉልህ ለውጦች ማምጣቱን ገልጸዋል።

ይህም አባል ሀገራት ጠንካራ የግብርና ዕቅድ ሥርዓት እንዲዘረጉ፣ ውጤታማ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም ቀረፃ እንዲኖራቸው እና በምርትና ምርታማነት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማገዙን አንስተዋል።
ፕሮግራሙ ትኩረት የሚያደርገው በተለይም በምርት መጠንና በምርታማነት ዕድገት ላይ በመሆኑ፤ በአሁኑ ወቅት በበርካታ ሀገራት ውስጥ የሚታየው የምርት መጠን መጨመር የዚሁ ጥረት ውጤት ነው ብለዋል።
ማንኛውም የልማት እንቅስቃሴ ከውኃ ጋር የተቆራኘ መሆኑን አስገንዝበው፤ ግብርናን፣ ኢነርጂን ወይም ጤናን ስናስብ ሁሉም ነገር ከውኃ ጋር የተያያዘ ነው፤ ስለዚህ ውኃ ለዘላቂ ልማት እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ለዚህም ነው “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” የሚለው መሪ ሐሳብ ለ39ኛው የሕብረቱ መሪዎች ጉባዔ የተመረጠው ብለዋል።
ኮሚሽነሩ ጉዳዩ በሕብረቱ አጀንዳነት የተያዘው በአህጉሪቱ ያለውን የውኃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ታስቦ መሆኑን አስረድተዋል።
በአህጉሪቱ ወደ 400 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች መሰረታዊ የውኃ አገልግሎት እንደማያገኙ ጠቁመው፤ ከ700 ሚሊየን የሚልቁትም ደኅንነቱ የተጠበቀ የጽዳት አገልግሎት የላቸውም ብለዋል።
ይህ የአገልግሎት እጥረት በሰዎች የዕድገትና የአህጉሪቱ የትራንስፎርሜሽን ጉዞ ላይ ትልቅ እንቅፋት መሆኑንም አመላክተዋል።
ውኃን እንደ ትምህርት፣ ጤና እና ግብርና ትልቅ ትኩረት ሰጥተን ብንሠራበት ኖሮ ይህንን ችግር በቀላሉ መፍታት እንችል ነበር ያሉት ኮሚሽነሩ፤ አሁን ላይ ጉዳዩ ትኩረት በማግኘቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ዋነኛ ግብ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ መሆኑን ተናግረው፤ የአፍሪካ ግብርና ልማት ፕሮግራም 45 በመቶ የሚሆነውን የግብርና ምርት በአፍሪካ ለማምረት ግብ ይዞ እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
በተጨማሪ የአፍሪካን የውኃ አካላት ሀብት ወይም ብሉ ኢኮኖሚን ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሆነ አንስተው፤ ይህ ዘርፍ ለአህጉሪቱ የሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ መነቃቃት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል ነው ያሉት።
የአፍሪካን የሰብል ዝርያዎች መጠበቅ መቻል የአህጉሪቱ ኅልውና ጉዳይ መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸው፤ ለዚህም ጠንካራ የዘር ባንኮች ሊኖሩን ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026