🔇Unmute
አዲስ አበባ፣ የካቲት 1 /2018 (ኢዜአ) ፦የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በስድስት ወራት ከተሞከሩ 27 ሺህ 773 የሳይበር ጥቃቶች 99 ነጥብ 03 በመቶ የሚሆነውን ማክሸፍ ተችሏል አለ።
ተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል።
የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀያየሩ የመጡትን የሳይበር ጥቃት ባህሪያት ግምት ውስጥ በማስገባት የመከላከል አቅማችን እየዘመነ ይገኛል ብለዋል፡፡
የሳይበር ደህንነት ሥጋቶችን ቀድሞ ለመለየትና ምላሽ ለመስጠት የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማቶችን ለማበልጸግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራተጂ መሠረት የሚሆኑ ተግባራት መከናወናቸውን ጠቅሰው የመንግሥት ተቋማትን ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ አሠራራቸውን ዲጂታላይዝ የሚያደርጉ የቴክኖሎጂዎችን እንዲታጠቁ መደረጉን ገልጸዋል።
ለአብነትም ገቢዎች ሚኒስቴር የኢ-ኢንቮይስ፣ አዲስ አበባ ገቢዎች የሰውነት ላይ ካሜራ፣ እንዲሁም ፌደራል ፖሊስ የተቀናጀ የሰው ሀብትና የሰነድ አስተዳደር ሲስተሞችን በማልማት አገልግሎታቸውን እንዲያዘምኑ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶችን ለማክሸፍ እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ በስድስት ወራት ከተሰነዘሩ 27 ሺህ 773 የሳይበር ጥቃቶች ውስጥ 99 ነጥብ 03 በመቶ የሚሆነውን ማለትም 27 ሺህ 505ቱን ማክሸፍ መቻሉን ገልጸዋል።
የዲጂታል ፎረንሲክ ምርመራን በተመለከተ አስተዳደሩ ከቀረቡለት 253 የምርመራ ጥያቄዎች ውስጥ ለ245ቱ ምላሽ መሰጠቱን የኢመደአ መረጃ አመልክቷል፡፡
የኢዜአ የዲጂታል ሚዲያ ገጾች ፦ https://linktr.ee/ENADigital
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026