🔇Unmute
ሞጆ ፤የካቲት 5/2018 (ኢዜአ)፡-በኦሮሚያ ክልል የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ የተጀመሩ ስራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ ገለፁ።
የሞጆ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመርቆ ወደስራ ገብቷል።

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲ ማዕከሉን መርቀው አገልግሎት ሲያስጀምሩ አንደገለጹት በክልሉ የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ ለዲጂታላይዜሽን ትኩረት ተሰጥቷል።
ለዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫን ተደራሽ ለማድረግ በመጀመሪያ ምዕራፍ በአዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ሸገር፣ ቢሾፍቱና ጂማ ከተሞች ወደስራ ማስገባቱን አስታውሰዋል።
ተግባሩን በማጠናከርም ወደ 26 ከተሞች እየተስፋፋ መሆኑን ጠቅሰው የዛሬ የሞጆ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ስራ መጀመር የዚሁ አካል መሆኑን አስረድተዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የህንፃ ግንባታውን በፍጥነት በማጠናቀቅ ከወረቀት ንኪኪ ነፃ የሆነ ዲጂታል አገልግሎት ማስጀመር መቻሉን ገልጸዋል።
የማዕከሉ ሙያተኞችም ህብረተሰቡን በስነ-ምግባርና በታማኝነት በማገልገል የአገልግሎት አሰጣጥ ዕርካታን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል ።
በሶስተኛ ምዕራፍ በክልሉ 60 ከተሞች የመሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ለማስጀመር ግብ መቀመጡን አንስተዋል።
በቀጣይ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን፣ የኮሪደር ልማት፣ የገቢ አሰባሰብና የልማት ስራዎች ማጠናከር ላይ በትኩርት ይሰራል ብለዋል።
የሞጆ ከተማ ከንቲባ አቶ ገዛሊ ሀሹ በበኩላቸው በከተማዋ መልካም አስተዳደርን በማስፈን ቀልጣፋ የህዝብ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ጥረት እይተደረገ ብለዋል።
ለዚህም በተለያዩ ተቋማት ሲሰጥ የነበረውን የመንግስት አገልግሎቶች በመሶብ የአንድ አገልግሎት ማእከል መስጫ በማሰባሰብ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር መዘርጋቱ አንስተዋል።
''ማዕከሉ የህዝቡ ዕንግልት ከማስቀረት ባለፈ የአገልግሎት አሰጣጥ ማነቆዎችን የሚቀርፍ ነው'' ያሉት ከንቲባው ጥራት ያለው ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እንዲቻል የማዕከሉ ሙያተኞችን በስነ ምግባር፣ በትምህርት ዝግጅት መመደቡን ተናግረዋል ።
ማእከሉ የ23 መስሪያ ቤቶች፣ በ12 መስኮቶች 106 አገልግሎቶች እየሰጠ ይገኛል ብለዋል።

የማእከሉን ስራ መጀመር አስመልክተው አስተያየት ከሰጡ የሞጆ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ አስቴር ቢራ እንደገለፁት ማእከሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ማዘመኑ እንግልትን የሚያስቀር ነው።
ይህም ጊዜና ገንዘባቸውን ከመቆጠብ ባለፈ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችን በአንድ ቦታ አገልግሎት ማግኘት እንደሚያስችላቸው ጠቁመዋል።
ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ ሙሉ ቸርነት በበኩላቸው መስተዳድሩ የህዝቡን ቅሬታ ለመፍታት መሶብ የአንድ ማእክል አገልግሎትን ስራ ማስጀመሩ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
ባንኮች ጨምሮ በአገልግሎት መስጫ ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ከመስሪያ ቤት ወደ መስሪያ ቤት የነበረውን ምልልስ በማሳጠር ፈጣን አገልግሎት እንድያገኙ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026