🔇Unmute
አዳማ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦በፌዴራልና በክልሎች መካከል ያለውን የጋራ ገቢ ክፍፍል ፍትሃዊ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ውጤት ማምጣታቸውን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አስታወቁ።
ምክር ቤቱ በበይነ-መንግሥታት የፌዴራል ግንኙነትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በመድረኩ ላይ እንዳስታወቁት፤ የምክር ቤቱ አንዱና ዋነኛው ተግባር ፍትሃዊ ልማትና ዕድገት እንዲኖር ማስቻል ነው።
ለዚህም ተፈጻሚነት ባለፉት አምስት ዓመታት አዳዲስ አሠራሮችን የመዘርጋትና ነባሮቹን የማሻሻል ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል ብለዋል።
በተለይም በጋራ ገቢዎች ክፍፍል ቀመር ላይ የተደረገው መሠረታዊ ማሻሻያ የክልሎችን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን ጠቁመዋል።
"ከማሻሻያው በፊት 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ብቻ የነበረው የክልሎች የጋራ ገቢ ድርሻ፤ በ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ወደ 91 ነጥብ 73 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ተደርጓል" ብለዋል።
ይህ ስኬት ሊመዘገብ የቻለው የገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ ዝውውርን የሚያፋጥን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት በመዘርጋቱና የምክር ቤቱን ውሳኔዎች በፍጥነት ወደ ተግባር በመቀየሩ መሆኑን አመልክተዋል።
ከዚህ ባለፈም ከከፍተኛ ማዕድን ሀብቶች የሚሰበሰበው የሮያሊቲ ገቢ ክፍፍልም መሻሻል ማሳየቱን ገልጸዋል።
ምንም እንኳ አመርቂ ውጤቶች ቢመዘገቡም አሁንም ያልተሻገርናቸው ተግዳሮቶች መኖራቸውን ያነሱት አፈ ጉባኤው፣ በተለይም ከፌዴራል ተቋማት ወደ ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች የሚተላለፉ ድጎማዎች ላይ የአሳታፊነትና የግልጸኝነት ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
ሥልጠናው እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላት እንደሚያግዝም አስረድተዋል።

በምክር ቤቱ የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ቋሚ ኮሚቴ ጸሐፊ አቶ ኃይሉ ኢፋ በበኩላቸው፤ ምክር ቤቱ የዜጎችን ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎችንና ግልጽ የአሠራር ሥርዓቶችን በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የስልጠና መድረኩም በሀብት ክፍፍል ሥርዓቱ ላይ መተማመንን በመፍጠር ለፌዴራል ሥርዓቱ መጠናከር የጎላ ሚና እንደሚኖረው አስታውቀዋል።
በመድረኩ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ በጀትና የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026