🔇Unmute
ወላይታ ሶዶ፤መጋቢት 9/ 2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የብሄራዊ ጥቅምና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ያለልዩነት በአቋም መስራት የግድ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለጹ።
የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ፣ ታሪክን፣ መልካአ ምድርን እንዲሁም ዓለም አቀፍ እውነታን በመያዝ የቀጠለ የዲፕሎማሲ ጥረት መሆኑ ይታወቃል።
ከአፍሪካ በህዝብ ብዛት በሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኢትዮጵያ ከባህር ተገፍታ እና ተገልላ መኖር የለባትም በሚል የባህር በር ጉዳይ የትውልድ ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል።
በአንድ ወቅት የባህር በር ባለቤት የነበረች ሀገር እንዴትና ለምን አጣች የሚለው ጉዳይም የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ የሚነሳ ጉዳይ ሆኗል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የብሄራዊ ጥቅምና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ያለልዩነት በአቋም መስራት የግድ መሆኑን ምሁራን ያስረዳሉ።
በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት አልማዝ ባልታ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ያለባህር መግቢያ መውጫ ህልውናዋ አደጋ ላይ የሚወድቅ በመሆኑ የትውልድ ጥያቄ ሆኖ መምጣቱ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል።
የህዝብ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ፤ የምጣኔ ሃብቷ በእጅጉ እያደገ መሆኑ እንዲሁም ቀጣናዊ ትስስርን ከማሳለጥ አንፃር ኢትዮጵያ የባህር መውጫና መግቢያ ያስፈልጋታል ብለዋል።
በመሆኑም ጥያቄው የተገቢነት ማሳያ የሚሆኑ ተጨባጭና አሳማኝ ምክንያቶች ያሉት በመሆኑ ተገቢው ምላሽ እስከሚሰጥ ድረስ ጥያቄያችን ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።
የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄው የብሄራዊ ጥቅምና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ያለምንም ልዩነት በጋራ የምንቆምለት አጀንዳችን ሆኖ መዝለቅ አለበት ብለዋል።
በዚህ ረገድ በተለይም ምሁራን በጥናትና ምርምር ጭምር የተደገፉ ጽሁፎችን በማሳተም የላቀ ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አንስተዋል።
በዩኒቨርሲቲው የቋንቋ እና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህርትና ተመራማሪ ደነቁ አበረ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ እየሄደችበት ያለው የዕድገት ግስጋሴ ከራሷ አልፎ ለቀጣናው አገራትም የጋራ ተጠቃሚነት ጉልህ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
በመሆኑም ጠንካራ ትስስር ለመፍጠር የባህር በር ማግኘቷ የግድ መሆኑን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ ካላት የህዝብ ብዛትና ለቀይ ባህር ካላት ቅርበት፣ ከታሪክና ከመልካአ ምድር አንፃር የባህር በር ማግኘት የትውልዱ ጥያቄ ሆኖ ቀጥሏል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ የብሄራዊ ጥቅምና የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ያለልዩነት በአቋም መስራት የግድ ይላል በማለት ምሁራኑ አፅኖት ሰጥተዋል።
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026
ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...
May 28, 2026