🔇Unmute
ሀዋሳ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅም በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ መሆኑን አምራች ኢንዱስትሪዎች ገለጹ፡፡
"ለኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ አውደ ርዕይና ባዛር ትናንት በሃዋሳ ተከፍቷል፡፡
በአውደ ርዕይና ባዛሩ ላይ የተሳተፉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት የማምረት አቅምን በማሳደግ በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና እያበረከተ ነው፡፡
ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል የአማረና ቤተሰቡ የተለያዩ ፈጠራ ማሽነሪ ስራዎች ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ አማረ ዓይነ-አበባው በኤግዚቢሽንና ባዛሩ ላይ የጫጩት መፈልፈያ ማሽን ይዘው መቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡
ማሽኑ 2 ሺህ እንቁላል በ21 ቀን ውስጥ ተፈጥሯዊ ሂደቱን ጠብቆ ወደ ጫጩትነት እንዲቀየር የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የፈጠራ ስራው ከውጭ ሲገባ እስከ 3 ሚሊየን ብር የሚሸጠውን ማሽን በ350 ሺህ ብር እንዲቀርብ በማድረግ የሃገርን የውጭ ምንዛሬ ያስቀረ ነው ብለዋል፡፡
መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የአምራች ኢንደስትሪው ተኪ ምርት የማምረት አቅም ማደጉን የገለጹት አቶ አማረ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በዘርፉ መነቃቃትን መፍጠሩን አመልክተዋል፡፡

የአበራ አብረሃም እንጨት ስራ ድርጅት ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስምኦን ታፈሰ በበኩላቸው ባለፉት ሶስት ዓመታት መንግስት ለኢንዱስትሪ ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት ተኪ ምርቶችን የማምረት አቅም እያደገ መጥቷል ነው ያሉት፡፡
ድርጅታቸው ከውጭ የሚገቡ የእንጨት ውጤት የሆኑ የቢሮ እቃዎችን በሃገር ውስጥ ምርት በመተካት በሃገር ኢኮኖሚ ላይ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በሲዳማ ክልል ለሚገኙ አብዛኞቹ የመንግስት ተቋማት የቢሮ እቃዎችን እንደሚያቀርቡ ገልጸው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሃገር ምርት የመጠቀም ባህልን እንዳሳደገ ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ ሰፊ የስራ እድልና የገበያ ትስስር እየተፈጠረ ሲሆን ባዛርና አውደ ርዕዮችም ተሞክሮ ለመለዋወጥና የገበያ አድማሱን ለማስፋት እንደሚያግዙ ነው የገለጹት፡፡
በኮሚፒዩተር አማካይነት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ማሽኖችን በመስራት የውጭ ምርቶችን በሃገር ውስጥ እንደሚተኩ የገለጹት ደግሞ የሪቨርስ ኢንጅነሪንግ ስራ አስፈጻሚ ኢኒጅነር በረከት መስፍን ናቸው፡፡

እንደ ሃገር የተጀመረውን የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተከትሎ በአምራች ኢንድስትሪው ዘርፍ ''መስራት ይቻላል'' የሚል መነቃቃት፣ከፍተኛ የስራ እድልና የገበያ ትስስር መኖሩን ተናግረዋል፡፡
ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ የሚሰሩ ዘመናዊ የመንገድ ዳር ፖሎችን ጨምሮ ሌሎች ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውንና በሀገር ኢኮኖሚ ላይም አበርክቶአቸው እያደገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአውደ ርዕይና ባዛሩ ከ160 በላይ አነስተኛና መካከለኛ ኢንደስትሪዎች ምርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን እስከ 60 ሚሊየን ብር የገበያ ትስስር እንደሚፈጠርም ከክልሉ ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ትናንት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የተከፈተው ባዛርና አውደ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ነው፡፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026