🔇Unmute
ባሕርዳር፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ በክልሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ እርካታን ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ።
የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አጋር ተቋማትን ያሳተፈ ወርክ ሾፕ በባህር ዳር ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊ የቻለ ይግዛው በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ የሚያደርጉ ቴክኖሎጂዎች ለምተው በተቋማት ተግባራዊ እንዲሆኑ ተደርጓል።

የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን በምርምር፣ በመፍጠር፣ በማልማትና በማሻሻል ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ስራዎች የማዋል ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት የግብርናውን ምርታማነት ለማሳደግ፣ የማዕድንና የቱሪዝም ብሎም ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎችን ማዘመን የሚያስችሉ አማራጭ ቴክኖሎጂዎችን ማቅረብ እየተቻለ ነው ብለዋል።
የዛሬው መድረክም የከፍተኛ ትምህርት እና የሌሎች ተቋማት ትስስርን የማጠናከር ዓላማ ያለው መሆኑንም አስረድተዋል።
የአማራ ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ልማትን ለማረጋገጥ ዘመኑ ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች በብዛትም ሆነ በጥራት መጠቀም ይገባል።
በተለይም የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ፣ ዲጂታል ኢኮኖሚን እውን በማድረግ፣ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየን(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ልማት ዘርፋን ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ነው ያሉት።
በዚህም የክልሉን የገቢ አሰባሰብ ያዘመነ ውጤታማ ቴክኖሎጂ ለምቶ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ብቃት ያላቸው ቴክኖሎጂዎችን በማልማትና በመጠቀም በትብብር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026