🔇Unmute
ሀላባ ፤መጋቢት 22/2018 (ኢዜአ)፡- በገጠር ኮሪደር ልማት ከጨለማ ወደ ብርሃን በመሸጋገር አዲስ የህይወት ምእራፍ በመጀመራችን ተደስተናል ሲሉ በሀላባ ዞን የሲምቢጣ ቀበሌ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ሀላባ ዞን የዌራ ዲጆ ወረዳ የሲምቢጣ ቀበሌ ነዋሪዎች በምሽት የብርሃን አድማስ ታጅበው መኖር ከጀመሩ ወራቶች እየተቆጠሩ ነው።

በድቅድቅ ጨለማ ህይወታቸውን ይመሩ የነበሩ አርሶ አደሮች አሁን ላይ ምሽቱን በብርሃን የሚረማመዱበት መንደር ሆኖላቸዋል።
በቀበሌው የሚኖሩት አርሶ አደር ገረመው መሀመድ እና ባለቤታቸው አሁን ላይ መሽቶ በጨለማ እንቸገራለን የሚል ስጋት የለም፤ “የጨለማ ህይወትም አብቅቷል” ይላሉ።
ልጆቻቸው ያለምንም ስጋት በምሽትም ይሁን በሌሊት መብራት አብርተው ማጥናት የቻሉበት፤ ተንቀሳቃሽ የእጅ ስልክ ያለ ሃይል እጦት መጠቀም የቻሉበት አጋጣሚ በመፈጠሩ መደሰታቸውን ይናገራሉ።
ለእኛም ለልጆቻችንም አዲስ ህይወት መኖር ጀምረናል የሚሉት አርሶ አደር ገረመው፤ የአኗኗር ዘይቤያቸው አሁን ላይ በመሰረታዊነት የተለወጠ በመሆኑ በጨለማ የኖርነው ህይወት የሚያስቆጭ ነው ይላሉ።

በቀበሌው የሚኖሩት አርሶ አደር ሎባ ባላ እና ወይዘሮ ፈዲላ አወል፤ ከጨለማ ህይወት ወጥተን በአዲስ ምእራፍ አዲስ ህይወት መኖር በመጀመራችን ተደስተናል ብለዋል።
በጓሯችን አትክልት፣ ፍራፍሬና አዝመራው፤ በቤታችን መብራቱ ተመቻችቶልን የመኖር እድል በማግኘታችን እኛም ይሁን ቤተሰባችን ደስተኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የከበደው የኑሮ ዘይቤ አሁን ላይ ምቹ እና ቀላል በመሆኑ ደስተኞች ነን ያሉት ነዋሪዎቹ በብርሃን የታጀበ አዲስ የህይወት ምእራፍ መኖር የጀመርን በመሆኑ ለዚህ ስኬት ላበቁን የመንግስት አካላት እናመሰግናለን ብለዋል።

የሲምቢጣ ቀበሌ ነዋሪዎችን የአኗኗር ዘይቤ ከጨለማ ወደ ብርሃን ብሎም ወደ ዘመናዊ አኗኗር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት በተጀመረው የገጠር ኮሪደር ልማት ነው።
በዚህ የልማት ኢንሼቲቭ በማእከላዊ ኢትዮጵያ የተለያዩ ወረዳዎች ተከናውኖ የበርካታ አርሶ አደሮችን ህይወት መለወጥ ያስቻለ ሆኗል።

የልማት ስራውን በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በማዳረስ የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ በመለወጥ የተሻለ ህይወት መምራት እንዲችሉ እየተደረገ ይገኛል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026