የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

Apr 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ መደረጋቸውን የክልሉ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ገለጸ።

በጎንደር ከተማ በ2ኛው ምዕራፍ ሁለተኛው ዙር መርሃ ግብር ታቅፈው ጥሪትና ሀብት በማፍራት ወደ ተሻለ ህይወት የተሸጋገሩ ከ4 ሺ በላይ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች ዛሬ ተመርቀዋል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የቢሮው ሃላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ/ር) እንደተናገሩት የክልሉ መንግስት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ከድህነት ለማውጣት የከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂዎችን ቀርጾ እየተገበረ ይገኛል፡፡

በክልሉ ጎንደር ከተማን ጨምሮ በ18 ከተሞች በአካባቢ ልማት፣ በቀጥታ ድጋፍ፣ በልዩ ድጋፍና በወጣቶች ፕሮጀክት ከ239 ሺህ 437 በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ የማድረግ ተግባር እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የክልሉ መንግስት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር ከ60 ቢሊዮን ብር በላይ መድቦ ሰትራቴጂካዊ የሆኑ የድህነት ቅነሳ የልማት ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

ለከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብርም በክልሉ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ ላለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት በመርሃ ግብሩ የተቃፉ የከተማ ነዋሪዎች ሀብትና ጥሪት አፍርተው ከተረጂነት እንዲወጡ የማድረግ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡

በጎንደር ከተማም ከ43 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በልማታዊ ሴፍቲኔት ታቅፈው በተለያዩ የልማት ተግባራት በማሳተፍ ኑሯቸውን እንዲያሻሽሉ የቁጠባና የስራ ባህላቸውንም እንዲያዳብሩ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ዜጎችን ከተረጂነት ከማውጣት ባሻገር ከተሞች የሚያከናውኗቸውን የልማት ስራዎች በማገዝ በኩል ትልቅ ፋይዳ አለው ያሉት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው ናቸው፡፡

በከተማው በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የታቀፉ ዜጎች በአካባቢ ጽዳት፣ በአረንጓዴ ልማትና በከተማ ግብርና ስራዎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

የከተማው ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የገንዘብ ቁጠባንና የስራ ባህል ለውጥ እንዳመጣ አግዞኛል ያሉት ደግሞ ወይዘሮ መልሽው ሃይማርያም ናቸው፡፡

በቆጠቡት መነሻ ገንዘብ አነስተኛ የዳቦ መጋገሪያና የመሸጫ ሱቅ ከፍተው ለስድስት ሰዎች የስራ እድል በመፍጠር ኑሯቸውን በመቀየር ከድህነት ለመውጣት እንደቻሉም አስረድተዋል፡፡

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ተጠቃሚ የሆኑት ወይዘሮ ፀሐይ አወቀ በበኩላቸው ሀብትና ጥሪት በማፍራት አሁን ላይ አንዲት የወተት ላም ገዝተው በየቀኑ 12 ሊትር ወተት ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የክልሉና የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ለመርሃ ግብሩ መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አጋር አካላትም የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው 

አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...

Jun 10, 2026

በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...

Jun 9, 2026

በፓርኩ ለአቮካዶ ዘይት አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርት የሚያቀርቡ ማህበራት ተጠቃሚ ሆነዋል

ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...

Jun 6, 2026

የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ ያነቃቃል

ነገሌ ቦረና፤ ግንቦት 19/2018(ኢዜአ)፦ የነገሌ ቦረና ገዳ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት መጀመር የአካባቢውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የበለጠ የሚያ...

May 28, 2026