የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

Apr 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

በጽህፈት ቤቱ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ ሂርባዬ በዞኑ በበልግ አዝመራ 294 ሺህ 389 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ዕቅድ ተይዟል ብለዋል።

እስካሁን በተካሄደው ስራም 260 ሺህ 780 ሄክታር መሬት በአራት ዋና ዋና ሰብሎች በዘር መሸፈኑን ገልጸዋል፡፡


የተጠቀሰው ሄክታር መሬትም በበቆሎ፣ በስንዴ፣ በጤፍ፣ በቦሎቄና በሌሎች ሰብል ዘር መሸፈኑን ገልጸው የግብርና ስራውን ለማሳካትም የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦቱም በወቅቱ ለአርሶ አደሩ መድረሱን ጠቁመዋል።

በዘር ከተሸፈነው መሬትም እስካሁን 239 ሺህ 230 ሄክታር በመስመር፣ 175 ሺህ 209 ሄክታሩ ደግሞ በኩታ ገጠም የእርሻ ስነ-ዘዴ መልማቱን አስታውቀዋል፡፡

በዞኑ ቆላማ አካባቢ የዝናቡ ስርጭት የሚቆየው ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ የዘር ስራውን ለማፋጠን በርካታ ትራክተሮች መሰማራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በበልግ አዝመራ ልማቱ ከ95 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች መሳተፋቸውን ተናግረዋል፡፡

ምርታማነቱን ለማሳደግም ከ95 ሺህ 403 ኩንታል በላይ ማዳበሪያና 42 ሺህ 262 ኩንታል የምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ መከፋፈሉንም አብራርተዋል፡፡

በዞኑ በበልግ አዝመራ ከሚለማው መሬትም ከ7 ሚሊዮን 175 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዷል ብለዋል፡፡


በዞኑ አዶላ ወረዳ የሞኤ ቦኮ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሹና ጎበና ለበልግ አዝመራ ያዘጋጁትን መሬት በዘር በመሸፈን ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ምርታማነታቸውንም ለማሳደግ የአፈር ማዳበሪያ ምርጥ ዘር መጠቀማቸውን ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ያለው ደጋ፣ ወይና ደጋና ቆላማ የአየር ጸባይ ለሰብል ልማትና ለእንስሳት እርባታ አመቺ መሆኑ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026