🔇Unmute
ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦በጅግጅጋ ከተማ ለበዓል ገበያ በቂ የእርድ እንስሳትና የግብርና ምርቶች አቅርቦት መኖሩን ሸማቾችና ነጋዴዎች ገለጹ።
በጅግጅጋ ከተማ ኢዜአ ያነጋገራቸው ነጋዴዎችና ሸማቾች ለዘንድሮው የትንሣዔ በዓል በከተማዋ በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች የፍጆታ ምርቶች አቅርቦትና ግብይት መኖሩን ገልጸዋል።
ወይዘሮ ሲሃም በድሪ በአትክልት ምርቶች ንግድ ላይ የተሠማሩ ሲሆኑ በበዓል ገበያው በቂ ምርት መኖሩን በመግለፅ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እያቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል።

በምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ አለመታየቱን እና በአሁን ወቅት በምርት አቅርቦት በኩል ችግር አለመኖሩን ገልጸዋል።
ከፍየል ነጋዴዎች መካከል ወይዘሮ አሚና ዩሱፍ በገበያው በቂ የእርድ እንስሳት መቅረቡን ተናግረዋል።
በእንቁላል ምርት ሽያጭ ላይ የተሠማሩት አቶ ታረቀኝ ጀምበሩ በበኩላቸው ለበዓሉ በቂ ምርት መኖሩን ጠቅሰዋል።
የጅግጅጋ ከተማ ንግድና ገበያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ ለይላ መሀመድ በበኩላቸው፤ ለትንሳኤ የበዓል ገበያ የግብርናና የፋብሪካ ምርቶች እጥረት እንዳይፈጠር ከህብረት ስራ ማህበራት ጋር በቅንጅት መሰራቱን አንስተዋል።
የበዓል ምርቶቹን በበቂ ሁኔታ ከማቅረብ ባለፈ ህገ ወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026