የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በሕብረት ሥራ ማህበራት የተካሄደው የሪፎርም ትግበራ ኢኮኖሚውን ማነቃቃትና ገበያን ማረጋጋት አስችሏል

Apr 22, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ኮምቦልቻ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦በሕብረት ሥራ ማህበራት የተካሄደው የሪፎርም ትግበራ ኢኮኖሚውን በማነቃቃትና ገበያን በማረጋጋት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሕብረት ሥራ ኮሚሽን “ቀበሌ የመድረስ ምዕራፍ” በሚል መሪ ሃሳብ 2ኛውን ሀገር አቀፍ የሕብረት ሥራ ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ በተለያዩ ከተሞች ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።

በኮምቦልቻ ከተማ መካሄድ በጀመረው መድረክ የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አምባዬ ወልዴ እንደገለጹት፣ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም የኅብረት ሥራ ማህበራት እንዲጠናከሩ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።


የኅብረት ሥራ ማህበራት የሪፎርም ሥራ ቀደም ሲል መተግበሩንና በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

ሪፎርሙ ኅብረት ሥራ ማህበራት አቅማቸው እንዲጠናከር፤ ዘመናዊ አሰራርን እንዲተገብሩ፣ ካፒታላቸውን እንዲያሳድጉ፣ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩና ግልፀኝነትና ተጠያቂነት እንዲያሰፍኑ ምቹ መደላድል መፍጠሩንም አመልክተዋል።

እንዲሁም ኢኮኖሚውን ከማጠናከር ባለፈ ገበያ በማረጋጋት ውጤት ማስመዝገብ እንደቻሉ ጠቅሰው፤ ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠልም "ቀበሌ የመድረስ ምዕራፍ" በሚል እንደሀገር በተለያዩ ማዕከላት ዛሬ የንቅናቄ መድረክ መጀመሩን ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ በክልሉ በሕብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ ነው ብለዋል።


እስከ ቀበሌ ያሉ ባለሙያዎችን በማብቃትና በመደገፍ ሪፎርሙን በሙሉ አቅም መተግበር እንደሚገባ ጠቁመው፣ ገበያን በማረጋጋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ በኩል ጅምር ውጤታማ ሥራ እንዳለ ገልፀዋል።

ሪፎርሙ የሕብረት ሥራ ማህበራትን አሰራር በሁለንተናዊ መንገድ በማዘመን፣ የቁጠባ ባህላቸውን በማሳደግ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ልምዳቸውን በመለዋወጥና ካፒታላቸውን በማሳደግ ውጤት እያመጣ ነው ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌትነት አማረ ናቸው።


የተገኘውን ውጤት በማስቀጠል ገበያውን ለማረጋጋት፣ ኢኮኖሚውን ለማሳደግና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የአፋር ክልል ማህበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱ ሀሰን በበኩላቸው፤ ሪፎርሙ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያስገኘውን ውጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ ነው ብለዋል።


መድረኩ ለስምንት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አመራሮች እንዲሁም የአማራና የአፋር ክልል የቀበሌ ሕብረት ሥራ ባለሙያዎችና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂ የማጠናከር ተግባራት እየተከናወነ ነው

ጅግጅጋ፤ ሚያዝያ 13/2018 (ኢዜአ)፦ የኅብረት ሥራ ማኅበራትን በቴክኖሎጂና ሌሎች መስኮች የማጠናከር ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሠ መ...

Apr 22, 2026

ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካውያን በምሳሌነት የሚጠቀስ ነው

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በስንዴ ልማት ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካዊያን በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን የአ...

Apr 15, 2026

በጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

አዶላ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን በበልግ አዝመራ ከ260 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ...

Apr 9, 2026

በክልሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተጠቃሚ ሆነዋል

ጎንደር፤ መጋቢት 24/2018( ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ከ239 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በከተሞች የምግብ ዋስትና ስትራቴጂ ተ...

Apr 3, 2026