የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኢንዱስትሪ ዐቅሞችን ለይቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥናትን መሠረት ያደረገ ተግባር እየተከናወነ ነው

Apr 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አርባ ምንጭ፤ ሚያዝያ 14/2018 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያሉ የኢንዱስትሪ ዐቅሞችን ለይቶ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥናትን መሠረት ያደረገ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ርዕሠ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ።

ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት እምቅ ዐቅም ፍኖተ ካርታ ላይ የሚመክር መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።


ርዕሠ መሥተዳድር ጥላሁን በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ዐቅሞችን ለይቶ በማልማት ጥቅም ላይ ለማዋል በጥናት ላይ የተመሠረተ ሥራ እየተሠራ ነው።


ለክልሉ ብሎም ለሀገር ሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ የአምራች ኢንዱስትሪው ሚና ጉልህ መሆኑን ገልጸው፤ በክልሉ በርካታ የኢንዱስትሪ አማራጮች እንዳሉ አመላክተዋል።

የለውጡ መንግሥት በተከተለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በርካታ ለውጦች መምጣታቸውንም ጠቁመዋል።

ማኑፋክቸርንግ ኢንዱስትሪው በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በተኪ እና ወጪ ምርቶች ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ አሳይቷልም ብልዋል።


ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የሰነቅነው ራዕይ እንዲሳካ በየደረጃው ያለው አመራር በኢንዱስትሪው ዘርፍ የበኩሉን አስተዋጾ እንዲያበረክትም አሳስበዋል።



የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴዔታ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው፤ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር የማይተካ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

መንግሥት ለኢንዱስትሪ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠቱ እና ተወዳዳሪ የሚያደርግ የኢንዱስትሪ ፖሊሲና ግልጽ መርሆዎች በማስቀመጡ ዘርፉ ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን አስረድተዋል።

ለዚህም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች በሙሉ ዐቅማቸው እንዲያመርቱ ከፍተኛ መነቃቃት መፍጠሩን ነው ያስረዱት።

በዚሁም የአምራች ኢንዱስትሪው የማምረት ዐቅም ከዚህ ቀደም ከነበረበት ወደ 66 ነጥብ 3 በመቶ ማደጉን አብራርተዋል።

ከተኪ ምርት አኳያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 4 ነጥብ 65 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ግምት ያለው ምርት መተካት እንደተቻለ ጠቁመው፤ በዘርፉ ከ202 ሺህ ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።


ክልሉ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ሰፊ ዐቅም ስላለው ሁሉም ኢንዱስትሪዎች በሙሉ ዐቅማቸው እንዲያመርቱ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰናይት ሰለሞን ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026