የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና የራስን አቅም የመገንባት ታሪካዊ ጉዞ ነው 

Apr 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፤ ሚያዝያ 15/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገርን የኢኮኖሚ ነፃነት በማረጋገጥ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ታሪካዊ ጉዞ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ይህን የተናገሩት "ድሬ ታምርት ኢትዮጵያ ትበልፅግ" በሚል መሪ ሃሳብ በተዘጋጀው የአምራች ኢንዱስትሪዎች ኤክስፖ የፓናል ውይይት ላይ ነው።


አቶ መላኩ በወቅቱም፤ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ በተደረገው ድጋፍና ክትትል እመርታዊ ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

በንቅናቄው የተዘጉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ በማድረግ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች በጥራትና በስፋት እየተተኩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት፣ አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ እና የስራ ዕድል በመፍጠር ረገድም መሠረታዊ ውጤቶች መገኘታቸውን በመጥቀስ።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገርን የኢኮኖሚ ነፃነት በማረጋገጥ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ታሪካዊ ጉዞ መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል።

በሌሎች ሀገራት አልባሳት፣ መድኃኒት፣ መገልገያዎችና ሌሎች ምርቶች ላይ ጥገኛ የሆነ አገር ሉዓላዊነቱን ማረጋገጥ እንደማይችል በማመላከት።

በንቅናቄው በተሰሩ ስራዎች በዘንድሮ በጀት ዓመት ብቻ 13 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገቡ የውጭ ሀገራት ባለሃብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በዘርፉ ለመሰማራት መዘጋጀታቸውን አስታውሰዋል።

ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግና በኢኮኖሚው ውስጥ የመሪነት ድርሻውን እንዲያረጋግጥ የህግና የፖሊሲ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ይገኛሉም ብለዋል።


የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፤ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በተደረጉ ድጋፎች ተዘግተው የነበሩ 15 ከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ማምረት በማሸጋገር ከ9 ሺህ 200 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን ገልጸዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎቹ ተኪ እና ወጪ ምርቶችን በስፋትና በጥራት እያመረቱ መሆኑን ጠቅሰው ከንቅናቄው በኋላ የኢንዱስትሪዎቹ የማምረት አቅም ከ42 በመቶ ወደ ወደ 64 በመቶ ከፍ ማለቱን አንስተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ፤ ባለፉት አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተሰሩ ስራዎች ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻላቸውን ገልፀዋል።


በተደረጉ ሁሉን አቀፍ ድጋፎችና ክትትሎች የተዘጉ እና በግንባታ ላይ ያሉ ፋብሪካዎች ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን በማስታወስ።

ባለፉት ዓመታት 253 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ከ2 ሺህ 620 በላይ ባለሃብቶች ፍቃድ ወስደው ወደ ዘርፉ መግባታቸውን ጠቅሰው ወደ ማምረት የተሸጋገሩትም ከ10ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ፈጥረዋል ብለዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ባለቤቶች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026