የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በምዕራብ ሸዋ ዞን በ960 ሄክታር መሬት ላይ የምርጥ ዘር ብዜት እየተከናወነ ነው

Jun 14, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አምቦ፤ ሰኔ 7/2018 (ኢዜአ) ፡-በምዕራብ ሸዋ ዞን በዘንድሮው የመኸር ወቅት የምርጥ ዘር አቅርቦትን በራስ አቅም ለመሸፈን በ960 ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ ምርጥ ዘሮችን የማባዛት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ምዕራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ካሉ ዋና ዋና የሰብል አምራች አካባቢዎች አንዱ ሲሆን፥ በተለይም እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍ እና ጥራጥሬዎች በስፋት ይመረቱበታል።

የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት በየዓመቱ የምርታማነት መጠንን ለመጨመር ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን ተደራሽ ለማድረግ ይሰራል።

በዞኑ የተጀመረው በ960 ሄክታር መሬት ላይ ምርጥ ዘርን የማባዛት ሥራ፥ ቀደም ሲል የነበረውን እጥረት በማስቀረት ዞኑ በምርጥ ዘር አቅርቦት ራሱን እንዲችል ለማድረግ ያለመ ነው።

ይህ ስትራቴጂ በዞኑ ውስጥ የሚገኙ የአፈር ዓይነቶችንና የአየር ንብረትን መነሻ በማድረግ የተመረጡና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የሰብል ዝርያዎችን በአካባቢው አባዝቶ በቀጥታ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ ያስችላል።

የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት የግብርና ሜካናይዜሽንና ግብዓት አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ዘሪሁን ጌትነት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተሻሻሉ ምርጥ ዘሮች ብዜትና ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ ነው።

በዞኑ በመኸር ወቅቱ ከፍተኛ ምርት የሚሰጡና በሽታን መቋቋም የሚችሉ የምርጥ ዘር ዝርያዎችን በ960 ሄክታር ማሳ ላይ በማባዛት 24 ሺህ 200 ኩንታል ምርጥ ዘር ለማግኘት ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል።

ከእነዚህም መካከል በቆሎ፣ ስንዴ፣ ጤፍ እና ሌሎች ሰብሎች እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት ከ130 ሄክታር በላይ ማሳ በበቆሎ ምርጥ ዘር መሸፈኑን የገለጹት አቶ ዘሪሁን፤ አርሶ አደሮቹ የግብርና ግብዓቶችንና የኤክስቴንሽን አሰራሮችን በተግባር እያዋሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የምርጥ ዘር ብዜቱ በደንዲ፣ ኢሉ ገላን እና ባኮ ቲቤ ወረዳዎች በሚገኙ የገበሬዎች ሕብረት ሥራ ዩኒየኖችና በሞዴል አርሶ አደሮች ማሳ ላይ በቅንጅት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በዘር ብዜት ሥራው ላይ ከ2 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ለሥራው ውጤታማነት ለአርሶ አደሮቹ ሥልጠና ከመስጠት ባለፈ ጽሕፈት ቤቱ በቅርበት የቴክኒክ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የዘር ብዜት ሥራ የአርሶ አደሩን የምርጥ ዘር እጥረት ከመቅረፍ ባለፈ፣ ለገበያ የሚቀርብ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ እንደሚሆንም አቶ ዘሪሁን አስረድተዋል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን በዘንድሮው የመኸር እርሻ በአጠቃላይ ከ900 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች እየለማ እንደሚገኝ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026