የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በምስራቅ ወለጋ ዞን የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል

Jun 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ነቀምቴ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ በምስራቅ ወለጋ ዞን የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።

በተለያዩ ወረዳዎች የተገነቡ እነዚሁ ፕሮጀክቶች የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ እና የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያግዙ ሲሆን ከ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ መሆናቸው ተገልጿል።

የምስራቅ ወለጋ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ አብዲሳ እንደገለጹት፤ በዞኑ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እያሳደጉ የሚገኙ የልማት ስራዎች ሰፊ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተከናወኑ ይገኛሉ።


በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአጠቃላይ 484 ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ታቅዶ ወደ ሥራ የተገባ ሲሆን፣ የአፈጻጸም ሂደቱም የተሻለ መሆኑን ተናግረዋል።

ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ በመጀመሪያ ዙር ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ 249 ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በሁለተኛው ዙር ደግሞ 178 የተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

ለአገልግሎት ክፍት ከሆኑትና በመጠናቀቅ ላይ ከሚገኙት ፕሮጀክቶች መካከል የመንግሥት መሥሪያ ቤት ሕንጻዎች እና የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ የመንገዶች፣ የድልድዮች እና የተለያዩ የጥገና ሥራዎች እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ተቋማት ይገኙበታል ብለዋል።

በተለይም የመንገድ መሠረተ ልማቱ ዞኑን ከሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ጋር በማገናኘት የንግድ እንቅስቃሴውን ለማሳለጥ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው አስረድተዋል።

ከነዚህም መካከል የነቀምቴ - ጊዳ - ቡሬ፣ ነቀምቴ - ሳሲጋ - ሶጌ እና የቢላ - ዘነጊ - ኡኬ መንገዶች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዞኑ ያለውን ሰፊ የውሃ ሀብት በመጠቀም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የመስኖ ልማት ሥራዎች በግንባታ ላይ እንደሚገኙም አስረድተዋል።

በተለይም የአንገር መስኖ እና የአርጆ መስኖ መሰረተ ልማቶች ተጠቃሽ ሲሆኑ፣ ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ 50 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

ከዞኑ ነዋሪዎች መካከል የጉቶ ጊዳ ወረዳ ነዋሪው አቶ ቴዎድሮስ ወጋሪ በሰጡት አስተያየት፤ ቀደም ሲል በመንገድ እጥረትና ብልሽት ምክንያት ይደርስባቸው የነበረው እንግልት ዘንድሮ መፍትሔ ማግኘቱን ተናግረዋል።

ሌላኛው ነዋሪ አቶ አበበ ፊሪሳ በበኩላቸው፣ መንግሥት የዜጎችን ተጠቃሚነት በማስቀደም የጀመራቸው የልማት ሥራዎች ከሌላው ጊዜ በተሻለ በፍጥነትና በጥራት መጠናቀቃቸው ተስፋ ሰጪ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተለይም አጎራባች ክልሎችንና ዞኖችን የሚያስተሳስሩ የመንገድና የመስኖ ሥራዎች የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ የሚያፋጥኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026