🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 18/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) አባል ለመሆን የምታደርገው የድርድር ሒደት አካል የሆነውን የሁለትዮሽ የገበያ ዕድል ፕሮቶኮል ከኒውዚላንድ ጋር ተፈራርማለች።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፉ የባለብዙ ወገን የንግድ ሥርዓት ለመቀላቀል ለምታደርገው ጉዞ ትልቅ ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑ ተገልጿል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ለረጅም ጊዜ ሲካሔድ የነበረውን የሁለትዮሽ ድርድር ያጠናቀቀው ይህ ስምምነት፣ በሸቀጦችና በአገልግሎት ዘርፎች ላይ በጋራ የተደረሱ የገበያ ተደራሽነት ግዴታዎችንና ጥቅሞችን ያካተተ ነው።
ፕሮቶኮሉን በጄኔቫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ እና አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው እና በዓለም ንግድ ድርጅት የኒውዚላንድ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ክሌር ኬሊ ፈርመውታል።

ይህ ስምምነት ሁለቱ አገራት ግልጽነት የሰፈነበት፣ በሕግ የሚመራ እና ልማትን ማዕከል ያደረገ የባለብዙ ወገን የንግድ ሥርዓት ለመገንባት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ መሆኑ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተመላክቷል።
የኒውዚላንድ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ክሌር ኬሊ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስመዝገብ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗን በማንሳት የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ስትሆን ከሌላው ዓለም ጋር የሚኖራትን የኢኮኖሚ ትስስር ለማጠናከር ዕድል እንደሚሰጣት ገልጸዋል።
አያይዘውም አገራቸው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደት በመደገፍ ረገድ የምታደርገውን አስተዋጽኦ አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም ስምምነቱ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር የተሻለ ዕድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።
አምባሳደር ፀጋአብ ከበበው በበኩላቸው በድርድሩ ሂደት ኒውዚላንድ ላሳየችው ገንቢ ተሳትፎ እና ቀጣይነት ላለው ድጋፍ ምስጋና ማቅባቸውን ኢዜአ ከስፍራው ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከሁለትዮሽ የንግድ ግንኙነቱ ባለፈ፣ ኢትዮጵያ እና ኒውዚላንድ በተለያዩ ዓለም አቀፍና ባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ ያላቸውን የቅርብ ትብብር አጠናክረው ቀጥለዋል።
በኒውዚላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እያደገ የመጣ ሲሆን፣ ግንኙነቱ በዋናነት በግብርና ትብብር፣ በጂኦተርማል (የእንፋሎት) ኃይል ድጋፍና በቴክኒክ አገልግሎቶች ላይ ያተኮረ ነው።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሁሉም ዘርፍ ለትውልድ የሚሻገር የላቀ ዕድገት እያስመዘገ...
Jun 24, 2026
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026