🔇Unmute
ሀዋሳ፤ ሰኔ 24/ 2018 (ኢዜአ):-የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ከሐይቁ የተፈጥሮ ውበት ጋር ተሰናስሎ በልዩ ዲዛይን በላቀ ጥራት እየተገነባ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለጹ።
የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው ለከተማዋ የኮሪደርና የሐይቅ ዳርቻ ልማት ሥራዎች የሚጠበቅባቸውን በመወጣት ታሪካዊ አሻራቸውን እንደሚያሳርፉ ገልጸዋል።
ሀገራዊ የኮሪደር ልማት ኢኒሺዬቲቭ መተግበር ከተጀመረ በኋላ ከተሞች ውብ ገፅታና ዘመናዊነትን ከመላበስ ባለፈ ለኑሮና ለንግድ እንቅስቃሴ ምቹ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
በሃዋሳ ከተማ ደግሞ ልማቱ ከተማዋ የቱሪስት መዳረሻነቷ ከፍ እንዲል፣ ለኑሮም ምቹ እንድትሆንና ውበቷም ይበልጥ እንዲጎላ እያደረጋት ነው።

በቅርቡም ከኮሪደር ልማቱ በተጨማሪ የተፈጥሮ ጸጋዎቿ እንዲገለጡ የሚያደርግና ከኮሪደር ጋር የተሰናሰለ የሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ተጀምሯል፡፡
ፕሮጀክቱን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንዳሉት፤ የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት ከሐይቁ የተፈጥሮ ውበት ጋር ተሰናስሎ በልዩ ዲዛይን በላቀ ጥራት እየተከናወነ ነው።
የሐይቅ ዳርቻ ልማቱ የከተማዋን የኮንፈረንስ ማዕከልነት እንዲሁም የጎብኚዎቿን የቆይታ ጊዜ እንደሚያራዝመው አንስተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የማህበረሰቡ አሻራ በጉልህ እንዲያርፍ ታስቦ መጀመሩን የገለጹት ከንቲባው 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት እንደተያዘለትና ህብረተሰቡም በአቅሙ አስተዋጽኦ በማድረግ የድርሻውን እንዲወጣ አመልክተዋል።
እንደ ከንቲባ ጥራቱ ገለጻ፤ በከተማዋ በ2ኛ እና በ3ኛ ዙር 8 ነጥብ 9 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ሥራ ተከናውኗል።
ልማቱም የብስክሌት፣ የሞተር ብስክሌትና የመኪና ማቆሚያዎች፣ የታክሲ መጫኛና ማውረጃ፣ የሕፃናት መጫወቻዎችንና የወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያዎች አካቶ የተከናወነ መሆኑንም አመልክተዋል።
በአሁን ወቅት 4 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው አራተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸው፣ ልማቱም ከሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ጋር መሰናሰሉን አመልክተዋል።
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ በከተማዋ እየተከናወኑ ባሉ የኮሪደርና የሐይቅ ዳርቻ ልማት ሥራዎች የሚጠበቅባቸውን በመወጣት ታሪካዊ አሻራቸውን እንደሚያሳርፉ አረጋግጠዋል።

ከነዋሪዎቹ መካከል ወይዘሮ ያምሮት ኃይሌ የኮሪደር ልማቱ ሀዋሳ ድሮ ከነበራት ውበት በላይ እንዳደመቃትና ተወዳዳሪ እንዳደረጋት ተናግረዋል።
በሆቴል ሥራ ዘርፍ የተሰማሩት አቶ ለገሰ ላሚሶ በበኩላቸው፤ በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ በተለይ የሆቴል ዘርፉ እንዲነቃቃ የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

ወደ ሀዋሳ የሚመጡ እንግዶችን በላቀ መስተንግዶ ተቀብለው ለማስተናገድ ይበልጥ መነቃቃታቸውን ገልጸው፣ የተጀመረው የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ተጠናቆ ከተማዋ ይበልጥ እንድታድግ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል፡፡
ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...
Sep 10, 2026
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...
Aug 13, 2026
ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...
Jul 30, 2026
ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...
Jul 30, 2026