🔇Unmute
ገንዳውኃ፣ ሰኔ 25/2018 (ኢዜአ):- በምዕራብ ጎንደር ዞን በመጪው መኸር ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሜካናይዜሽን እንደሚለማ የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የግብርና ባለሙያዎችና አልሚ ባለሀብቶች የተጀመረውን የሜካናይዜሽን እርሻ እንቅስቃሴ ለመገምገምና ለማበረታታት በመተማ ወረዳ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።
በጉብኝቱ ወቅትም የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ እንደገለጹት፤ ዞኑ ገበያ ተኮር የግብርና ምርቶች የሚመረቱበት መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህም ሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ጥጥ፣ ቦሎቄ፣ ማሽላና ሌሎች የሰብል አይነቶችን በዓይነትና በብዛት በማምረት፣ በወጪ ንግድ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ምርታማነትን ለማሳደግም አልሚ ባለሀብቶችና አርሶ አደሮች የተሻሻለ ዘርና ማዳበሪያን ከመጠቀም ባሻገር፣ በምርት ማምረትና አሰባሰብ ወቅት ዘመናዊ የግብርና አሰራርን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል።
የዞኑ መስተዳድርም ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት ሰላሙን በማስጠበቅ፣ የነዳጅና የግብርና ግብዓት አቅርቦትን በማሻሻል ረገድ እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊና ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አንዳርጌ ጌጡ በበኩላቸው፤ ዞኑ ሰፊ መሬት፣ ተስማሚ ስነ ምህዳርና የአየር ጸባይ የታደለ በመሆኑ ለእርሻ ኢንቨስትመንት ተመራጭ መሆኑን አስረድተዋል።
በዚህም በአጠቃላይ ከ529 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓትና ለውጭ ገበያ የሚሆኑ ምርቶችን በስፋት ለማምረት እየተሰራ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከሚለማው መሬት ውስጥ ከ400 ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆነውን በሜካናይዜሽንና በኩታ ገጠም ለማልማት ታቅዶ፣ እስካሁን 250 ሺህ ሄክታሩን በዘር መሸፈን መቻሉን ተናግረዋል።
ይህም ምርታማነትን በማሳደግ፣ የምርት ብክነትን በመቀነስና ጥራት ያለው ምርትን በማምረት የወጪ ንግዱን ለማሳላጥ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።
በመተማ ወረዳ ኮኪት አካባቢ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩት አቶ ሳኒ እንድሪስ በበኩላቸው፤ በሜካናይዜሽን በመታገዝ የግብርና ልማት ስራቸውን እያከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ያወጡት የነበረውን ወጪና ያባክኑት የነበረውን ጉልበት ለመቀነስ እንደቻሉ አስረድተዋል።
በዘንድሮው የሰብል ልማት የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በስፋት ለመጠቀም መዘጋጀታቸውን የገለጹት ደግሞ በወረዳው በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩት ባለሀብትና አርሶ አደር አቶ ደምስ ሽታ ናቸው።
ከመንግስት በኩል እየተደረገ ያለው የጸጥታ ጥበቃና የቴክኒክ ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።
በመተማ ወረዳ በኮኪት ከተማና አካባቢዋ የተጀመረውን የተቀናጀ የሜካናይዜሽን እርሻ ንቅናቄ ወደ ሌሎች ወረዳዎች ለማስፋት እየተሰራ መሆኑንም ከመምሪያው የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በሁሉም ዘርፍ ለትውልድ የሚሻገር የላቀ ዕድገት እያስመዘገ...
Jun 24, 2026
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦የዕቃ ማከማቻ ደረሰኝ ሥርዓት ደንብ የግብርና ኢኮኖሚ ሽግግርን በማሳለጥና የገጠር ልማትን በማጎልበት አርሶ አደሮችን ተጠ...
Jun 10, 2026
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ በመዲናዋ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማላቅ የተገልጋዮችን እርካታ የሚያሳድጉ ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደ...
Jun 9, 2026
ሀዋሳ ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ማቀነባበሪያ ፓርክ ከአምራች ኢንዲስትሪዎች ጋር በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ...
Jun 6, 2026