የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት

በዞኑ የአቮካዶ ዓመታዊ የምርት መጠን ከነበረበት 600 ኩንታል ወደ 2 ሚሊዮን ኩንታል አድጓል

Jul 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

መቱ ፤ ሐምሌ 3/ 2018 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ለአቮካዶ ልማት በተሰጠው ትኩረት፣ ዓመታዊ የምርት መጠኑን ከነበረበት 600 ኩንታል ወደ 2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማሳደግ መቻሉን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

በኢሉባቦር ዞን ቀደም ሲል የነበረው የአቮካዶ አመራረት በአብዛኛው ልማዳዊ፣ ለረጅም ዓመታት ምርት የማይሰጥና በበሽታዎች የሚጠቃ በመሆኑ አርሶ አደሩ ከዘርፉ የሚያገኘው ጥቅም አነስተኛ ነበር።

ይህንን ክፍተት ለመሙላት የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በሽታን የሚቋቋሙ፣ ፈጣንና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን የማባዛትና የማስተዋወቅ ስራ በስፋት ሲያከናውን ቆይቷል።


አርሶ አደሩም ከባህላዊ አሰራር ወጥቶ ዘመናዊ የኩትኳቶ፣ የውሃ አጠቃቀምና የክምችት አያያዝ ዘዴዎችን እንዲከተል መደረጉ ከፍተኛ የምርት እድገት እያስገኘ ነው።

የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኜ ፍቅሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የዞኑን ምቹ የአየር ንብረትና መልክዓ ምድር በመጠቀም፣ የአቮካዶ ልማት በልዩ ኢንሼቲቭ ተቀርጾ በኩታገጠም አሰራር በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።


ከአምስት ዓመታት በፊት በዞኑ ይመረት የነበረው ዓመታዊ የአቮካዶ ምርት ከ600 ኩንታል የማይበልጥ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ዳኜ፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ስራው በልዩ ኢንሼቲቭ መመራት ከጀመረ ወዲህ ግን የምርት መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ አድጎ ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሊሻገር መቻሉን ገልጸዋል።

ለዚህ ከፍተኛ የምርት ዕድገት ዋነኛው ምክንያት በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርት መስጠት የሚችሉ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎች ለአርሶ አደሩ በስፋት መሰራጨታቸው መሆኑን ምክትል ኃላፊው አብራርተዋል።

መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት በዞኑ የአቮካዶ ልማት መሬት ስፋት ከነበረበት 500 ሄክታር በአሁኑ ወቅት ወደ 54 ሺህ ሄክታር ማደጉንም ምክትል ኃላፊው ገልጸዋል።

ይህንኑ የልማት ተግባር አጠናክሮ ለማስቀጠል በዞኑ በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች ላይ በተለየ ሁኔታ የማስፋፋት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዳኜ፤ በአሁኑ ክረምትም 5 ሺህ 900 ሄክታር መሬት ላይ የአቮካዶ ችግኝ በኩታ ገጠም አሰራር የሚተከል መሆኑን አስታውቀዋል።

በዞኑ በአቮካዶ ልማት ላይ ከተሰማሩት የበቾ ወረዳ አርሶ አደሮች መካከል አቶ ይማም ዓለሙ፤ ከልማቱ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት መቻላቸውን ጠቅሰው፤ ይህም ለምግብ ዋስትና መረጋገጥና ለኑሮዋቸው መሻሻል ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል።


በተመሳሳይ አርሶ አደር ተሾመ ጽጌ እና ድሪባ ገመቹ ፤ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን ማልማት ከጀመሩ ወዲህ የተሻለና ከፍተኛ ምርት ማግኘት መቻላቸውን ገልጸዋል።

አርሶ አደሮቹ ከመደበኛ የእርሻ ሥራቸው ጎን ለጎን በአቮካዶ ልማት ላይ በመሳተፍ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት መቻላቸውንና በዚህም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።

በኢሉባቦር ዞን በአሁኑ ወቅት ከ44 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች በአቮካዶ ልማት ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ከዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል በቂ የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶች ቀርበዋል

ባህር ዳር ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የእርድ እንስሳትና ሌሎች ምርቶችን በበቂ መጠን ለተጠቃሚው ማቅረብ መቻሉን የክ...

Sep 10, 2026

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው

ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ...

Aug 13, 2026

በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ ናቸው

ሮቤ፣ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦በባሌ ዞን በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን የብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ዓለ...

Jul 30, 2026

በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰዉ (ዶ/ር)

ሆሳዕና ፤ ሐምሌ 22/2018 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ...

Jul 30, 2026